ትራምፕ በስምምነቱ አተገባበር ደስተኛ ካልሆኑ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠነቀቁ

📌 Diğer 📰 Ethiopia 🕐 2 saat önce
ትራምፕ በስምምነቱ አተገባበር ደስተኛ ካልሆኑ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠነቀቁ

ለቡድን ሰባት ጉባዔ ፈረንሳይ የሚገኙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረሰው ስምምነት “ገና እንዳልተገባደደ” ጠቅሰው በመግባቢያ ሰነዱ አተገባበር ደስተኛ ካልሆኑ ቴህራን ላይ ጥቃት መፈጸም እንደሚቀጥሉ አስጠነቀቁ። “የመግባቢያ ሰነድ ነው፤ ካልወደድኩት መተኮስ እና ቦምብ መጣል እንቀጥላለን። ጥሩ ባህሪ ካላሳዩ በድጋሚ ድብደባውን እንቀጥላለን” ብለዋል።

አሜሪካ እና ኢራን ከሦስት ወራት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም የደረሱበት የመግባቢያ ስምምነት መፈረምን ዓለም በጉጉት እየተጠባበቀው ነው። የቡድን ሰባት አገራት በሁለቱ አገራት መካከል ተከታታይ እና ጠንካራ ስምምነት ሊደረስ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ወሳኙ የመግባቢያ ስምምነት በኢራን እና በአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በስዊትዘርላንዷ የመዝናኛ ስፍራ በርገንስቶክ ውስጥ ከነገ ወዲያ አርብ ይፈረማል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

ከሁለቱ አገራት እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ እና ዋነኛው ተደራዳሪ ሞሐማድ ባግሄር ጋሊባፍ እና የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ስምምነቱን በመፈረም ይፋ እንደሚደያርጉ ተነግሯል።

ጦርነቱን ያስቆማል የተባለውን የመግባቢያ ሰነድ በተመለከተ የተለያዩ ይዘቶች እየወጡ ቢሆንም ይፋዊ የስምምነቱን ሃሳብ የያዘው ሰነድ ገና ይፋ አልተደረገም።

የአሜሪካ እና የኢራን ባለሥልጣናት ስዊትዘርላንድ ውስጥ የሚገናኙት ስምምነቱን ለመፈረም ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይም ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በድርድሩ ቁልፍ ጉዳይ የሆነው የኢራን የዳበሩ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ መሥሪያ ግብአቶች ጉዳይ እንደሚገኝበት ተነግሯል።

📌 Kaynak

Bu haber XML kaynağından derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
📱
News AI World — Mobil uygulama
Bu haberleri 45 dilde, anlık çeviriyle cebinde. Erken erişim için Gmail adresini bırak.
← Tüm haberlere dön