ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሕዳሴው ግድብ ጉዳይን "ቅድሚያ ሰጥተው" እንደሚመለከቱት ተናገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን አለመግባባት "ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተው" እንደሚመለከቱት እና ፍትኃዊ የሆነ መፍትሄ እንደሚፈልጉለት ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በፈረንሳይ በተካሄደው እና ረቡዕ በተጠናቀቀው የቡድን ሰባት አባል አገራት ስብሰባ ወቅት ከግብፅ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተገናኙበት ጊዜ ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን አለመግባባት "ቅድሚያ ሰጥተው" እንደሚመለከቱት እና ፍትሐዊ የሆነ መፍትሄ እንደሚፈልጉለት ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በፈረንሳይ በተካሄደው እና ረቡዕ በተጠናቀቀው የቡድን ሰባት አባል አገራት ስብሰባ ወቅት ከግብፅ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተገናኙበት ጊዜ ነው።
አሜሪካን ጨምሮ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ጣልያን እና ካናዳ አባል በሆኑበት እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት በተካተተበት የበለጸጉ አገራት ስብስብ በሆነው የቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ ከአፍሪካ የግብፅ እና የኬንያው መሪ ተሳትፈዋል።
በዚህ ጉባዔ አጋጣሚ ትራምፕ ከአል ሲሲ ጋር በጋዜጠኞች ፊት ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ የተገነባው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ "በግብፅ ላይ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ አውቃለሁ" ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የሕዳሴ ግንባታን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከሱዳን እና ግብፅ ጋር አለመግባበት ውስጥ ቆይታለች።
ግብፅ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለአስራ አራት ዓመታት በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ሲደራደሩ የነበረ ቢሆንም ሦስቱንም አገራት የሚያስማማ ሁሉን አቀፍ መግባባት ላይ መድረስ አልተቻለም።
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አጠናቅቃ ያስመረቀችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከ5000 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌትሪክ ኃይል ያመነጫል።
ትራምፕ በተለያዩ ጊዜያት ስለ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ተቃራኒ የሆነ አቋም ሲያራምዱ እና ለግብፅ ወግነው አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል።
በጥር ወር ፕሬዝዳንቱ ለግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አል ሲሲ በጻፉት ደብዳቤ የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ ድርድር ለመጀመር እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዚህ ደብዳቤያቸው ላይ "በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን 'የአባይን ውሃ መጋራት' ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት መንፈስ ለመፍታት ዝግጁ ነኝ" ብለው ነበር።
ኢትዮጵያ በዚህ ለግብፅ በቀጥታ በተጻፈ ደብዳቤ ላይ የተጠቀሰችው በግልባጭ እንዲደርሳት ብቻ ነው።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንሳይ ተገናኝተው ሲወያዩ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ነው።
ፕሬዝዳንት አልሲሲ የአባይ ወንዝ ጉዳይ ለግብፅ ያለውን ጠቃሚነት ተናግረው ትራምፕ ጉዳዩን ለመፍታት ፍላጎት በማሳየታቸው አመስግነዋል።
"ከግብፅ ፕሬዝዳንት ጋር በመገናኘቴ ክብር ይሰማኛል" ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "እሱ በመላው ዓለም የተከበረ ሰው ነው። ግንኙነታችን ጠንካራ ነው። የግል ግንኙታችንም ለረዥም ጊዜ እንዲሁ ጠንካራ ነው" ሲሉ አል ሲሲን አሞካሽተዋል።
ትራምፕ አክለውም "በግድቡ ፕሮጀክት ጉዳይ እያገዝኩት ነው፤ በጋራ እየሠራንበት ነው" በማለት በጥምረት እየሠሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።
"ኢትዮጵያ ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ነው ግብፅን እና የግድቡን ጉዳይ እያስተናገደች ነው ያለችው" ያሉት ትራምፕ፣ ከግብፅ ጋር ከአባይ ባሻገር በንግድ ጉዳዮችም አብረው እንደሚሠሩ ጠቅሰዋል።
"የናይል ውሃ መሆን ከነበረበት መጠኑ ዝቅ እያለ ነው ያለው። . . .በኢትዮጵያ ግድብ ተገንብቷል። ብዙ ችግር በግብፅ ላይ እያደረሰ እንደሆነ አውቂያለሁ" ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የግድቡን ጉዳይ ፈትተውት እንደነበር ጠቅሰው ነገር ግን "በተጭበረበረ ምርጫ" ተሸንፈው ነገሮች መበላሸታቸውን ተናግረዋል።
በመቀጠልም "እስኪ በድጋሚ ነገሩን እናየውና ችግሩን እንፈታዋለን" ሲሉ ለአል ሲሲ ቃል ገብተዋል።
በትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አሸማጋይነት ተከታታይ ድርድሮች በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል መደረጋቸው ይታወሳል።
ነገር ግን ከስምምነት ተደርሶ ይፈረማል በተባለበት በመጨረሻው ሰዓት ኢትዮጵያ የቀረበው ስምምነት ጥቅሟን የሚጎዳ መሆኑን በመግለጽ ባለመፈረሟ ቱ ጉዳዩ በእንጥልጥል ቀርቷል።
በዚህም ምክንያት የተቆጡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በወቅቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ ከነበረው ድጋፍ የተወሰነው እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በፈረንሳዩ ውይይት ወቅት የግብፁ ፕሬዝዳንት ለትራምፕ ትልቅ ክብር እንዳላቸው እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም አምጥተዋል በሚል ምስጋና አቅርበዋል።
"ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለእርስዎ ያለኝን ክብር እና አድናቆት ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል። ይሄ ግድብ በግብፅ ላይ እየፈጠረ ያለውን እክል ስለመረዳትዎ ታላቅ አክብሮት አለኝ።"
ግብፅ እና ሱዳን በተደጋጋሚ በአባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ የገነባችው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በምሥራቅ የናይል ተፋሰስ አገራት ላይ ዘላቂ ስጋት ደቅኗል ሲሉ ይከስሳ
📌 Kaynak
Bu haber XML kaynağından derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →