በምርጫው ብልፅግና ዕጩ ባላቀረበባቸው ክልሎች የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ተፎካካሪዎች አሸነፉ

📌 Diğer 📰 Ethiopia 🕐 4 saat önce
በምርጫው ብልፅግና ዕጩ ባላቀረበባቸው ክልሎች የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ተፎካካሪዎች አሸነፉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ ያፀደቃቸውን የምርጫ ውጤቶች ይፋ ሲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ገዢው ፓርቲ ብልፅግና አብዛኞቹን መቀመጫዎች አሸንፏል። ብልፅግናን ጨምሮ ሦስት ፓርቲዎች በተወዳደሩበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አማሮ ኬሌ ምርጫ ክልል ኢዜማ አሸንፏል። ቦርዱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ይፋዊ ውጤት ሰኔ 14/2018 ዓ.ም. እንደሚገለጽ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ ያፀደቃቸውን የምርጫ ውጤቶች ይፋ ሲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ገዢው ፓርቲ ብልፅግና አብዛኞቹን መቀመጫዎች አሸንፏል።

ብልፅግናን ጨምሮ ሦስት ፓርቲዎች በተወዳደሩበት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አማሮ ኬሌ ምርጫ ክልል ኢዜማ አሸንፏል።

በዚህ የምርጫ ክልል የኢዜማ ዕጩ ሆነው የቀረቡት አቶ አወቀ አምዛዬ በ40.6 በመቶ ድምፅ ተፎካካሪዎቻውን ማሸነፍ ችለዋል።

አወቀ አምዛዬ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫም በዚሁ የምርጫ ክልል ያሸነፉ ሲሆን፤ የአካባቢውን ሕዝብ ለሁለተኛ ጊዜ በእንደራሴዎች ምክር ቤት ይወክላሉ።

የምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ አበባን ጨምሮ 40 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 35 ለክልል ምክር ቤት አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድምጽ ካገኙባቸው 17 የምርጫ ክልሎች መካከል በ16ቱ ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ አላቀረበም።

በኦሮሚያ ክልል ጎማ 2 ምርጫ ክልል የተወዳደሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 97.5 በመቶ በላይ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።

ከእርሳቸው ጋር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትኅ (ኢዜማ) እና የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ዕጩዎች ተወዳድረው ነበር።

ብቻቸውን በኦሮሚያ ክልል ያለ ተፎካካሪ የተወዳደሩት የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ዲማ ኖጎ እና አራርሶ ቢቂላ አሸንፈዋል።

ሰኔ10 ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል አምስት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች አሸናፊዎች ተለይተዋል።

በኮፈሌ 2 ምርጫ ክልል ብቻቸውን የተወዳደሩት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ እጩ ሰለሞን ታፈሰ አሸንፈዋል።

ብልፅግና ፓርቲን ወክለው በነቀምቴ የተወዳደሩት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ በ92 በመቶ ድምፅ አሸንፈዋል።

የዘጠኝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸናፊዎች የተለዩበት አማራ ክልል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተወዳደሩበትን ባሕር ዳር ምርጫ ክልልን ጨምሮ አራቱን ብልፅግና ሲያሸንፍ ሦስቱን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አሸንፏል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ በገርጨጭ እና የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ደግሞ በሳይንት 2 አንድ አንድ መቀመጫ አሸናፊ ሆነዋል።

ባለፈው ሣምንት ይፋ በተደረገ የምርጫ ውጤት በአማራ ክልል ጎንደር ዙሪያ 4 የተወዳደሩት የአብኑ ጣሂር መሐመድ አሸንፈዋል። ይሁን እንጂ በዚህ ምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዕጩ አላቀረበም ነበር።

በእስቴ 1 ከአብን ፓርቲ ጋሻው መርሻ 76.5 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። በዚህ የምርጫ ክልል አራት ፓርቲዎች የተወዳደሩ ሲሆን፤ ብልፅግና ግን አልተወዳደረም።

የአብን ዕጩ የሆኑት መልካሙ ፀጋዬም እንዲሁ በላይጋይንት 1 የምርጫ ክልል ሲያሸንፉ ከብልፅግና ፉክክር አልገጠማቸውም።

በኩታ በር የምርጫ ክልልም እንዲሁ ብልፅግና ሳይወዳደር የአብኑ የሱፍ ኢብራሂ በ70 በመቶ ድምፅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ማግኝት ችለዋል።

በሳይንት 2 ምርጫ ክልል ብቻቸውን የተወዳደሩት የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ እጩ ሙሐሙድ ቡሽራ ምንም እንኳ ለመምረጥ 35,924 መራጮች ቢመዘገቡም 9,577 ድምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን ቦርዱ አውጇል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስድስት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጤቶች የፀደቁ ሲሆን፤ ሦስቱን ብልፅግና ቀሪዎችን ሦስት መቀመጫዎች ደግሞ ኢዜማ በአማሮ ኬሌ፣ የጌዲዮ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በወናጎ እንዲሁም የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በሶዶ ዙሪያ አሸንፈዋል።

አራት የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውጤቶች የፀደቁበት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለቱን ብልፅግና ፓርቲ ሲያሸንፍ፤ ኢዜማ እና ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ደግሞ አንድ አንድ ወንበሮችን ማግኘት ችለዋል።

ተፈራ ጀበሮ በሎማ ቦሳ ምርጫ ክልል ካለ ብልፅግና ዕጩ ከስድሰት ፓርቲዎች ጋር ተፎካክረው በ33.5 በመቶ ድምፅ ነው ያሸነፉት።

በማጀት መደበኛ የምርጫ ክልል ደግሞ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ እና የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቱ ብቻ ተወዳድረው የነእፓ እጩ ብርሃኑ ሚስል በ34 በመቶ ድምፅ አሸንፈዋል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 መቀመጫዎች ያሏት አዲስ አበባ እስካሁን በምርጫ ቦርድ ፀድቆ ይፋ የሆኑ ሁለት ወንበሮች ብቻ ናቸው።

ብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበበት በምርጫ ክልል 11 የግል ተወዳዳሪ የሆኑት አበበ ገመቹ 17.6 በመቶ ድምፅ አሸንፈዋል። ምንም እንኳ በዚህ ምርጫ ክልል ገዢው ብልፅግና ዕጩ ባያቀርብም አሸናፊውን የግል ተወዳዳሪ ጨምሮ 10 የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን ተወዳድረዋል።

በምርጫ ክልል 25 ከብልፅግና ጋር ስምንት ፓርቲዎች የተፎካከሩ ሲሆን የብልፅግና ዕጩ የሆኑት የሺመቤት ነጋሽ በ51 በመቶ

📌 Kaynak

Bu haber XML kaynağından derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
📱
News AI World — Mobil uygulama
Bu haberleri 45 dilde, anlık çeviriyle cebinde. Erken erişim için Gmail adresini bırak.
← Tüm haberlere dön