በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 10 saat önce
በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል።

የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው።

ሙዚቃ ስሜት ነው የሚለው ፀሐዬ፣ "ከትክክለኛው ሙዚቃ ምን አጥተው ነው እንደዚህ የሚሠሩት?" ሲልም ይጠይቃል።

በኮምፒዩተር ተጠንቶ የተሠራ የኤአይ ሙዚቃ ለወረት ይሠራ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ ይሆናል የሚል ሃሳብም የለውም።

ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ "ኤአይ በተለይ አዳዲስ የሙዚቃ ሥራዎችን ለመሥራት በሃሳብም ሆነ በቴክኒክ ጥሩ አጋዥ ነው" ሲሉ በበጎ ተመልክተውታል።

ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው እሁድ ኤአይ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ አቤኔዘር ጌታቸው "ይህ የቴክኖሎጂ ክስተት ለሙዚቃ ዲሞክራሲን ያመጣ ነው" ይላል።

ኤአይ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ እና የገንዘብ አቅም ላላቸው ምዕራባውያን እና ብዙ የሚነገር ታሪክ እና ባህል እያላቸው ለመሥራት አቅሙ ለሌላቸው አፍሪካውያን እኩል ዕድልን እንደሰጠም ያምናል።

ሙዚቀኛዋ ብሌን ዮሴፍም ቴክኖሎጂው የራሱ የሆነ ጥቅም እና ጉዳት እንዳለው ጠቅሳ አዳሰስ ሥራዎችን ለመሥራት እንደ አጋዥ መጠቀሙ የባለሙያውን ጊዜ ለመቆጠብና ፈጠራን ለማገዝ እንደሚረዳ ታስረዳለች።

ኤአይ በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ የሰዎችን የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብትን ለመንጠቅ መሣሪያ በመሆን በይበልጥ ይኮነናል።

ሁለቱም ባለሙያዎች በዚህ ይስማማሉ። ይህ ግን ቴክኖሎጂው በመፈልሰፉ ሳይሆን ያለ አግባብ ጥቅም ላይ በመዋሉ የመጣ ችግር እንደሆነ ይገልጻሉ።

ብሌን "በሕይወት ያሉም ሆነ የሌሉ ድምጻውያን የሌላቸውን ተፈጥሮ በማላበስ እና አዲስ ማንነት በመፍጠር ያለፈቃድ የሰዎችን ማንነት እየነጠቀ ነው" ትላለች።

"ባለቤት አልባ የኤአይ ሙዚቃዎች እየጎረፉ ነው" የምትለው ብሌን፣ ይህን መቆጣጠር አለመቻሉ አሳዛኝ እንደሆነ ትናገራለች።

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ሲነሳ ስሙ በግንባር ቀደምትነት የሚነሳው አለማየሁ እሸቴ ባለቤት ወ/ሮ አየሁ ከበደም የባለቤታቸው ሥራዎች በኤአይ ተሠርተው መስማታቸው ካሳዘናቸው መካከል ይገኙበታል።

"በማን አለብኝት ታዛቢ የሌለው አስመስለው ሙዚቃውን እየተጫወቱበት ነው ያለው። ለማን አቤት ይባላል?" ሲሉም ይጠይቃሉ።

"ፈቃድ እንኳን ሳይጠይቁ አስመስለው ይሠራሉ። እኛም ወዴት ሄደን እናመልክት፣ ኮፒራይት ይከበር ተባለ ግን ውጤቱን አናውቀውም" ይላሉ በምሬት።

ኤአይ አዲስ የቴክኖሎጂ ክስተት እንደመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገራት የባለቤትነትን መብት የሚጠብቁበት እና የሚቆጣጠሩበት ሕግ የላቸውም።

በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር በቅጅ እና ተዛማች መብቶች የሮያሊቲ አስተዳደር አመራር ድምጻዊ ኃይሌ ሩትስ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን መልክ ለማስያዝ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ይገልጻል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ እስካሁን የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ባለመሆኗ በተለይ በዲጂታል የሚሠራጩ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነትን ማስጠበቅ ሳይቻል ቀርቷል።

የዓለም ንግድ ድርጅት አባል መሆን የተለያዩ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን፣ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስጠበቅ አንደኛው ነው።

ከኤአይ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ድንበር ተሻጋሪ የባለቤትነት ጥያቄዎች (ኮፒ ራይት) ጉዳዮች የሚታዩትም በዚሁ ዓለም አቀፍ የሕግ ማዕቀፍ ነው።

በአዋጁ ማሻሻል ላይ የኤአይ ጉዳይ መነሳቱን የጠቀሰው ድምጻዊ ኃይሌ፣ የወጥ ሥራዎች መብት መጠበቅ በሕጉ እንዲካተት ተደርጎ እየመጣ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የሙዚቃ ሥራዎች በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ ለንግድ ትርፍ ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስችል ሥርዓት እየዘረጋን ነው ብሏል።

ይህንን ከአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር ሆነው ለማስመረቅ እና ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን በመገለፅም በኤአይ የሚሠሩም ሆኑ ሌሎች ሥራዎች ወደ ሕግ ማዕቀፍ እንደሚገቡ አስረድቷል።

እንደ ስፖቲፋይ ያሉ ሌሎች የሙዚቃ ማሰራጫዎች እና ማውረጃዎች የባለቤትነት መብትን መጠበቅ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ዘርግተዋል።

የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኩ - ዩቲዩብ - ባለፈው ዓመት ወጥነት ለሌላቸው እና ከሌሎች ለተቀዱ ሥራዎች ክፍያ መፈፀም እንደሚያቆም ገልጿል።

ይህ የሌሎች ሰዎች የሙዚቃ ሥራዎች በኤአይ ተቀናብረው መቅረባቸውን ባያስቆምም፣ በኤአይ የተቀናበሩ ወጥ ሥራዎች ለአድማጮች እንዲቀርቡ ያበረታታ ይመስላል።

ድምጻዊያን ሥራዎቻቸውን ለአድማጭ ለማድረስ ዓመታትን ይገብራሉ። የተሻለ ሥራ ይዞ ወደ አድማጭ ለመድረስ የአቀናባሪዎችን ወረፋ መጠበቅ፣ ፕሮዲዩሰሮችን መፈለግ ይጠበቅባቸዋል።

አቀናባሪዎችም ከስቱዲዮዋቸው ሳይወጡ ቀኑን እና ሌሊቱን ያሳልፋሉ። በዚህም ዘመን የማይሽራቸውን የሙዚቃ ሥራዎች አበር

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön