አሜሪካ እና ኢራን በባሕረ ሰላጤው አካባቢ የተኩስ ልውውጥ አደረጉ
የአሜሪካ ጦር ኢራን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የተኮሰቻቸውን አራት ድሮኖች መትቶ መጣሉን አስታወቀ። ኢራንም በአጸፋው በኩዌት የሚገኙ ሁለት የአሜሪካ ጦር መቀመጫዎች ላይ ባለስቲክ ሚሳዔል ተኩሳለች። በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት የኢራን እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ተከትሎ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ወሽመጥን “ለነዳጅ እና ጋዝ ላኪዎች ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት” ዛተ።
በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ሁለቱ አገራት የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ እስላማዊ አብዮታዊ ዘቡ በሰጠው ማስጠንቀቂያ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለነዳጅ እና ለጋዝ ላኪዎች ሙሉ በሙሉ ቢዘጋ “ኃላፊነቱን የምትወስደው አሜሪካ ናት” ብሏል።
የአሜሪካ ጦር ኢራን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የተኮሰቻቸውን አራት ድሮኖች መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ፤ ጎሩክ እና ቃሽም በተባሉ ደሴቶች ላይ የኢራን የባሕር ዳርቻ ጥበቃ ማዕከላት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።
ኢራንም በአጸፋው በኩዌት የሚገኙ ሁለት የአሜሪካ ጦር መቀመጫዎች ላይ ባለስቲክ ሚሳዔል ተኩሳለች። በባሕሬን በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይም ጥቃት ማድረሷ ተገልጿል።
የባሕሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢራን ያደረሰችውን ጥቃት “በጽኑ” እንደሚያወግዝ አስታውቋል። በባሕሬን እንዲሁም በኩዌት ላይ የደረሰውን ጥቃት “ግልጽ ጸብ አጫሪነት” ብሎታል።
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →