ባለፈው ምርጫ ብልጽግናን ከወከሉ የአዲስ አበባ ተመራጮች ውስጥ ከ60 በመቶ በላዩ በአዲስ ተተኩ

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 25.03.2026
ባለፈው ምርጫ ብልጽግናን ከወከሉ የአዲስ አበባ ተመራጮች ውስጥ ከ60 በመቶ በላዩ በአዲስ ተተኩ

ብልጽግና ፓርቲ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአዲስ አበባ ከተማ ካቀረባቸው 154 ዕጩዎች ውስጥ 96 ያህሉ በባለፈው ምርጫ በመዲናዋ ያልተወዳደሩ እንደሆኑ ቢቢሲ ያደረገው ዳሰሳ ያሳያል። በመጪው ምርጫ በአዲስ አበባ ዕጩ ሆነው ካልቀረቡት ተመራጮች መካከል ምክትል ከንቲባው ጃንጥራር አባይ ይገኙበታል።

በ2013 ዓ.ም. በተደረገው አጠቃላይ ምርጫ ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው በአዲስ አበባ ከተመረጡት የፓርላማ እና የከተማ ምክር ቤት ተመራጮች ውስጥ 62 በመቶው በአዲስ ተተኩ። በመጪው ምርጫ በአዲስ አበባ ዕጩ ሆነው ካልቀረቡት ተመራጮች መካከል ምክትል ከንቲባው ጃንጥራር አባይ ይገኙበታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን ጨምሮ በርካታ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ በተወካዮች ምክር ቤት አዲስ አበባን እንዲወክሉ እንዲወዳደሩ በዕጩነት ቀርበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአዲስ አበባ ከተማ ካቀረባቸው 154 ዕጩዎች ውስጥ 96 ያህሉ በባለፈው ምርጫ በመዲናዋ ያልተወዳደሩ እንደሆኑ ቢቢሲ ያደረገው ዳሰሳ ያሳያል።

በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ከተመረጡ 160 ግለሰቦች ውስጥ በዚህኛውም ምርጫ ዕጩ ሆነው የቀረቡት 58 ያህሉ ብቻ ናቸው።

ቢቢሲ የተመለከተው የዕጩዎች ዝርዝር እንደሚያመለክተው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲወዳደሩ ያቀረባቸው ዕጩዎች 20 ናቸው። ከዚህ ውስጥ በድጋሚ ለዚህ ስፍራ ዕጩ የሆኑት አራቱ ብቻ ናቸው።

ፓርቲው ባለፈው ምርጫ ለፓርላማ ዕጩ ያላቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር የሆኑት ዳንኤል ክብረት በግል በተወዳደሩበት "ምርጫ ክልል 28" ነበር።

በዘንድሮው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ዳንኤል ክብረት አልተካተቱም። ብልጽግና ፓርቲም የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ሌሊሴ ነሜን በምርጫ ክልሉ ዕጩ አድርጎ አቅርቧል።

ፓርቲው ዕጩ ካላስመዘገበባቸው ሦስት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች ውስጥ በሁለቱ የሚወዳደሩት የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አመራሮች ናቸው።

በየካቲት መጨረሻ በተካሄደው የኢዜማ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው መሪ ሆነው የተመረጡት ኢዮብ መሣፍንት ብልጽግና ዕጩ ባላቀረበበት "ምርጫ ክልል 18" ይወዳደራሉ። በዚሁ ጉባኤ ምክትል መሪ የሆኑት ንጋቱ ወልዴ ደግሞ በ"ምርጫ ክልል 23" የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላስመዘገበበት ሌላኛው "ምርጫ ክልል 11" ከሚወዳደሩ ፖለቲከኞች መካከል ደግሞ በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የተመረጡት ዶ/ር አበባው ደሳለው ይገኙበታል።

በባለፈው ምርጫ በአማራ ክልል የወከሉትን ፓርቲ የለቀቁት ዶ/ር አበባው፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲን (ኢሕአፓ) ተቀላቅለዋል። አሁን ዕጩ ሆነው የቀረቡትም ኢሕአፓ የሚገኝበትን "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" የተሰኘ ቅንጅትን በመወከል ነው።

ገዢው ፓርቲ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እንዲወዳደሩ ካቀረባቸው 134 ዕጩዎች ውስጥ ባለፈው ምርጫም ለዚህ ስፍራ የተወዳደሩት 51 ያህሉ ብቻ ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እንዲሁም የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በድጋሚ ዕጩ የሆኑት የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።

በአሁኑ የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ካልተካተቱት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ ከመስከረም 2014 ዓ.ም. አንስቶ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው እያገለገሉ ያሉት ጃንጥራር አባይ ናቸው። ምክትል ከንቲባው በዘንድሮ ምርጫ የሚወዳደሩት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን "መቄት 1" ለክልሉ ምክር ቤት ነው።

በአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ሞጋች ጥያቄዎችን በማቅረብ የሚታወቁት የብልጽግና ተመራጩ ዶ/ር ሲሳይ መንግሥቴም የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ የሉም። በተመሳሳይ ጥያቄ አቀራረባቸው የሚጠቀሱት እና ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ ያሉት ዶ/ር ካሳ ተሻገርም ተተክተዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት አመራር የነበሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ካሳ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በዕጩነት ያልቀረቡ የአዲስ አበባ ተመራጮች ናቸው።

በ2016 ዓ.ም. ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታነት የተነሱት ንጉሡ ጥላሁን፣ ከአገር የሸሹት የቀድሞው ሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን እንዲሁም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ዶ/ር ዮናስ ዘውዴም ከተተኩ የቀድሞ ባለሥልጣናት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

አዲስ አበባን ወክለው ፓርላማ ተመራጭ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዘንድሮ ዕጩ የሆኑት ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ነው።

ብልጽግና ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ አበባን እንዲወክሉ ካቀረባቸው 20 ዕጩዎች

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön