ወራት የቀሩት ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 27.10.2025
ወራት የቀሩት ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰባት ወር በኋላ በአገሪቱ ይካሄዳል ላለው ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቷል። በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ያሉትን ግጭቶች እና አለመረጋጋት በመጥቀስ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከምርጫው በፊት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ እያሉ ነው። በቀጣዮቹ ወራት ግጭቶችን በማስቆም ለምርጫ አመቺ ሁኔታን መፍጠር ይቻላል ወይ በሚለው ላይም እርግጠኞች አይደሉም። ምን አማራጭ አለ?

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ለውይይት አቅርቧል።

ምርጫ ቦርድ ሰኞ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም. ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ዝግ ስብሰባ የዘንድሮውን ምርጫ ለማካሄድ የያዛቸውን ዕቅዶች በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስቀምጧል።

ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው የምርጫ ጽሕፈት ቤቶችን ከማደራጀት ጀምሮ እስከ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ድረስ ያሉትን ተግባራት የሸፈነ ነው።

ይህም የምርጫ አስፈፃሚዎች ምልመላዎች ይካሄድበታል ካለው ከጥቅምት 17 ጀምሮ የምርጫው አጠቃላይ ውጤት ይፋ ይሆንባታል ብሎ እስካቀደበት ሰኔ 3/2018 ዓ.ም. ድረስ የሚዘልቅ ነው።

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጋብዞ የነበረው በዚህ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት ለማድረግ አልሞ የነበረ ቢሆንም ከፓርቲዎች የቀረበውን የጊዜ ሰሌዳ ወደ ጎን ያሉ ጠንካራ ሃሳቦችን አስተናግዷል።

ፓርቲዎቹ ከረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው በፊት የሚቀድሙ ሌሎች መልስ የሚያሹ አንገብጋቢ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች መኖራቸውን አንስተዋል።

ቦርዱ ያቀረበው የመወያያ አጀንዳም አቅጣጫውን ለውጦ በአብዛኛው በአገሪቷ ባለው የፀጥታ ችግር ላይ ያጠነጠነ እንደነበርም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገልጸዋል።

ስብሰባው "በቦርዱ እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የተካሄደ ሳይሆን የፀጥታ አካላት የሚወያዩ ይመስል ነበር" ሲሉ አንድ ተሳታፊ ስለነበረው ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር እንደተናገሩት በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይቱን የተካፈሉ ሲሆን፣ ወደ አርባ የሚደርሱ ተናጋሪዎችም ሃሳብ ሰጥተዋል።

አብዛኞቹ የተሰነዘሩ ሃሳቦች መጪውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች አለመኖር ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ፣ አገሪቷ አሁን ያለችበት ሁኔታ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ ለማሳካት እንደማይችል ተሳታፊዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም ከምርጫው በፊት ወሳኝ የሆነውን የአገሪቷ የፀጥታ ችግርን ጨምሮ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ፓርቲዎቹ አስምረውበታል።

ፓርቲዎቹ ያነሷቸው ስጋቶች አወዛጋቢ ከነበረው እና የግጭት መካረር መነሻ ከሆነው 6ኛው አገራዊ ምርጫ አስቀድሞም ሲነሱ የነበሩ ናቸው።

ከአንድ የሥልጣን ዘመን በኋላም በአዳዲስ አካባቢዎች ግጭቶች ተቀስቅሰው እና በአገሪቷ ውስጥ ያለው የፀጥታ ችግር ሳይፈታ የዚህ ዓመቱ ምርጫ የወራቶች ዕድሜ ቀርቶታል።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀ መንበር የሆኑት ዶ/ር ራሔል ባፌ፣ ምርጫ ቦርድ ለውይይት ያቀረበው ሃሳብ "ቦርዱ እና ፓርቲዎች የተለያየ ክፍለ ዓለማት ላይ ነው ወይ የምንኖረው የሚል ጥያቄ የፈጠረ ነው" ብለዋል።

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች ግጭቶች ባሉበት፣ በሌሎችም አካባቢዎች የሰላም እጦት በሚታይበት ሕዝቡ ለአምስት ዓመት የሚመራውን መሪ ይመርጣል ተብሎ የጊዜ ሰሌዳ እስከ ማውጣት መደረሱ እንዳስገረማቸውም ዶ/ር ራሔል አክለዋል።

"በሕይወት የመኖር መብቱ ያልተረጋገጠለት ብዙ ዜጋ ነው ያለው፤ ሌላው ቀርቶ ውሃ ለመቅዳት፣ እንጨት ለመልቀም ደኅንነት የማይሰማው ሕዝብ ነው ያለው" ያሉት ዶ/ር ራሔል፣ ከምርጫው በፊት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አንስተዋል።

ከፍተኛውን የምክር ቤት መቀመጫ የሚይዙት ክልሎች በግጭት ውስጥ አሊያም በጦርነት ማግስት ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ጌትነት፣ "ይህ በሆነበት ሁኔታ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት አምጥቶ ሕጋዊ መንግሥት መመሥረት ይቻላል የሚል እምነት እንደሌላቸው" ገልጸዋል።

በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ ያለው አለመረጋጋት እና ግጭት በሌላውም አካባቢ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር በመግለጽም፣ በመላ አገሪቱ ሰላም እንዳለ ማሰብ አይቻልም የሚሉ ሃሳቦችም መሰንዘራቸውን አቶ ጌትነት ተናግረዋል።

"የባለፈው ምርጫም መንግሥት የላችሁም ከሚባል የሚያነክስ መንግሥት ይኑረን በሚል ብልጽግናን ተሸክመን ነው ያለፍነው" ያሉት አቶ ጌትነት፣ በዘንድሮም ምርጫ ይህ እንዲደገም እንደማይፈልጉ ፓርቲያቸውን ጨምሮ ከበርካቶች ጽኑ አቋም ተንጸባርቋል ብለዋል።

ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ካልቻለም በ2019 ዓ.ም. "አገር ላይኖር ይችላል" የሚል ስጋቶችም መነሳታቸውንም አቶ ጌትነት ጠቅሰዋል።

አገሪቷ ያለችበት ሁኔታ እንደሚያሳስበው በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው መግለጫዎች መግለጹን ያስታወሱት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፀሐፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬም፣ ከምርጫው በፊት መቅደም ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ያምናሉ።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታጠቅ አሰፋ "የአገሪ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön