በምሥራቅ አርሲ ሦስት ወረዳዎች በነዋሪዎች እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰው ምንድን ነው?
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገረ ስብከት ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። የአካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ደያረጉ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደር ባለሥልጣናት ደግሞ ስለተፈጸመው ጥቃት እና ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገረ ስብከት ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ።
የአካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ደያረጉ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደር ባለሥልጣናት ደግሞ ስለተፈጸመው ጥቃት እና ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ የቢቢሲ ምንጭ ጥቃቱ እሁድ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም. መጀመሩን ተናግረው ስልጣና ወረዳ ልዩ ስሙ በቼቶ በተባለ አካባቢ ሁለት፣ አሰኮ ወረዳ ደግሞ 11 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
እኚሁ ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የቢቢሲ ምንጭ በጥቃቱ የ101 ዓመት እድሜ ያለው "ጠለታ ገብርኤል" ቤተ ከርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት የአርሲ እና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባወጡት መግለጫ በምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች "13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውን እና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን" አመልክተዋል።
በተጨማሪም ካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም በተባለው ቤተ ክርስቲያን ላይ "ዘረፋ" መፈጸሙን የገለጹት ጳጳሱ "ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል" ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።
በአካባቢው ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች "በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸው እና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል" ሲሉም አስታውቀዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በአካባቢው የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ሌላ ግለሰብ በበኩላቸው በጥቃቱ ሚኒሻ የነበረው ወንድማቸው መገደሉን ገልጸው "ቤተክርስቲያኑ [ጠለታ ገብርኤል] ከታቦተ ሕጉ ውጪ ሙሉ በሙሉ ወድሟል" ብለዋል።
የአገረ ስብከቱ ምንጭ ግንቦት 23/2018 በነበረ ጥቃት ደጀሰላሙ ተቃጥሎ የነበረው ኩፍቴና መድሃኒዓለምን ግንቦት 24 ለ25 አጥቢያ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መቃጠሉን ጨምረው ገልጸዋል።
በጥቃቱ የተገደሉት ሟቾቹ ነዋሪዎች መሆናቸውን የተናገሩት እኚህ ግለሰብ በአሰኮ ወረዳ 280 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ጨምረው ተናግረዋል።
ቢቢሲ በደረሰው ጥቃት ላይ መረጃ ለመጠየቅ ለኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሶሪ ወጊን ስለተፈጸመው ጥቃት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ላቀረበላቸው ጥያቄ "እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም፤ እናጣራለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካበቢዎች አንዱ የሆነው የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድም ሰዎች ስለሞቱበት እና ንብረት ስለወደመበት ክስተት "መረጃ የለንም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ከጥቃቱ ጋር ስሙ እየተነሳ ያለው መንግሥት በሽብርተኝነት ፈርጆ ሸኔ ሲል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ጂሬኛ አያና ረቡዕ ዕለት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በጽሑፍ በሰጡት ምላሽ በምሥራቅ አርሲው ጥቃት የሠራዊቱ እጅ የለበትም ሲሉ አስተባብለዋል።
"በአሰኮ የተከሰተው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሌለበት የሆነ ነገር ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ በፍጹም አልተሳተፈም፣ አይሳተፍምም" ብለዋል።
የምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ከፍያለው ሸንቁጤ "እዚያ አካባቢ ትንሽ እርስ በርስ አለመስማማት አለ" በማለት ግድያዎች እየተፈጸሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ምርጫ መካሄዱን በማስታወስ በእነዚህ አካባቢዎች "እርስ በርስ መጨራረስ" የተደረሰው "ምርጫውን ለማደናቀፍ ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት ስለመኖሩ አለመታወቁን" ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥቃቱ የተፈጸመው በምን ምክንያት እና በማን እንደሆነ ለይቶ ለመናገር አሁን እንደማይችሉ ጨምረው አስታውቀዋል።
በአካባቢው የፀጥታ አካላት እና የሚያጣራ ቡድን ማክሰኞ ዕለት ግንቦት 25/2018 ዓ.ም. መሰማራቱን ተናግረው ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን ገልጸዋል።
በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን በተመለከተም "ግማሹ ዘጠኝ ይላል፤ ግማሹ ሰባት ይላል ይሄም ራሱ መጣራት አለበት" ብለዋል።
በአካባቢው ግንቦት 23 እና 24 የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተ ጥቆማ እንደደረሰባቸው መረጃው እንዳላቸው የሚናገሩት
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →