ኢራን ከተነገረው በላይ በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ቢቢሲ አረጋገጠ

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 4 gün önce
ኢራን ከተነገረው በላይ በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ቢቢሲ አረጋገጠ

ኢራን ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ስምንት አገራት ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላትን ዒላማ አድርጋ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን፣ በአየር ላይ ነዳጅ የሚሞሉ አውሮፕላኖችን እና ራዳሮችን በመምታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ውድመት አድርሳለች። ኢራን በአሜሪካ የጦር ተቋማት ላይ ያደረሰችው ጉዳት ከተነገረው በላይ መሆኑን የቢቢሲ ምርመራ አረጋግጧል።

ኢራን ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 20 የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን እና የደረሰው ጉዳት በይፋ ከታወቀው ከፍተኛ መሆኑን የቢቢሲ መረጃ ማጣሪያ የሆነው ቢቢሲ ቬሪፋይ የተነተናቸው የሳተላይት ምሥሎች እና ቪዲዮዎች አመለከቱ።

ኢራን ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ስምንት አገራት ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላትን ዒላማ አድርጋ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን፣ በአየር ላይ ነዳጅ የሚሞሉ አውሮፕላኖችን እና ራዳሮችን በመምታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ውድመት አድርሳለች።

ኢራን የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃቶችን ለመበቀል ባለፉት ሦስት ወራት በኢራቅ እና በሊባኖስ ያሉትን ጨምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና የጋራ ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ አድርጋለች።

የአሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት (ፔንታገን) ኤፒክ ፊዩሪ ባለው ዘመቻ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በኢራን ውስጥ ከ13 ሺህ በላይ ዒላማዎች መመታታቸውን ገልጿል።

አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ፣ ማክሰኞ ዕለት ባስተላለፉት መግለጫ፣ መካከለኛው ምሥራቅ ለአሜሪካ ጦር ሰፈሮች "አስተማማኝ ቦታ" እንዳልሆነ በመጥቀስ የአገራቸው ሠራዊት የአሜሪካን ሠራዊትን በማጥቃት ረገድ ስኬታማ እንደነበር አጉልተው ተናግረዋል።

አሜሪካ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች የኢራን ጦር ኃይል ከመደምሰስ አፋፍ ላይ ደርሷል በማለት ደጋግሞ ቢናገርም፣ ተንታኞች እንደሚሉት ግን በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የታየው ጉዳት የቴህራን መልሶ ማጥቃቶች የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከዚህ በፊት ካመኑት በላይ ዒላማውን የጠበቁ እና መጠነ ሰፊ ናቸው።

አንድ የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣን "ለወታደራዊ ዘመቻዎች ደኅንነት" ሲባል በቢቢሲ ቬሪፋይ ግኝቶች ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አሜሪካ ዋነኛ የሳተላይት ምሥሎች አቅራቢ የሆነው 'ፕላኔት' የተባለው ተቋም የኢራን እና በአብዛኛው የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢዎች የሚያሳዩ ምሥሎችን "ላልተወሰነ ጊዜ" ላለማቅረብ ገደብ እንዲያስቀምጥ በመጠየቅ የግጭቱን የሳተላይት ትንተና ለመገደብ ጥረት አድርጋለች።

ኩባንያውም ምሥሎቹ "በተቀናቃኝ ኃይሎች የአሜሪካ አጋሮችን እና የኔቶ አባላትን እንዲሁም ሲቪሎችን ዒላማ ለማድረግ" ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለማድረግ እንደሚፈልግ በመግለጽ የዕገዳውን ትክክለኝነት ደግፎታል።

ቢቢሲ ቬሪፋይ በኢራን ጥቃቶች ምክንያት በአሜሪካ ተቋማት ላይ የደረሱትን ጉዳቶች ለመተንተን ከሌሎች ዓለም አቀፍ የሳተላይት ምሥል አቅራቢዎች የተገኙ ምሥሎችን እንዲሁም ከፕላኔት ደግሞ ቆየት ያሉ ማነጻጸሪያ ምሥሎችን ተጠቅሟል።

በኢራን ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወታደራዊ ተቋማት የሚገኙት በሳዑዲ አረቢያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በኳታር፣ በኩዌት፣ በኢራቅ፣ በዮርዳኖስ፣ በባህሬን እና በኦማን ነው። የጥቃት ዒላማ የሆኑት ማዕከላት ትክክለኛው አሃዝ ከፍተኛ ሊሆን የሚችል ቢሆንም፣ አንዳንድ ተንታኞች ቁጥሩን አስከ 28 ያደርሱታል።

ጉዳት ከደረሰባቸው ውድ ወታደራዊ መሳሪያዎች መካከል በአረብ ኤምሬትስ ውስጥ በሚገኙት አል ሩዋይስ እና አል ሳድር አየር ኃይል ሰፈሮች ውስጥ እንዲሁም ዮርዳኖስ በሚገኘው ሙዋፋቅ ሳልቲ አየር ኃይል ሰፈር ውስጥ የነበሩ እጅግ ዘመናዊ የፀረ ባለስቲክ ሚሳዔል መከላከያ መሳሪያዎች ይገኙበታል።

አሜሪካ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች ውስጥ የተተከሉ ስምንት ታድ የሚባሉ የሚሳዔል መከላከያዎች ሲኖሯት እያንዳንዱን ለማምረት 1 ቢሊዮን ዶላር ያስወጣል።

እነዚህ የፀረ ሚሳዔል መከላከያዎች እያንዳንዳቸው 100 የሚሆኑ ወታደሮች ባለው ቡድን የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ በአንድ ዙር የሚተኩሷቸው ፀረ ሚሳዔሎች 12.7 ሚሊዮን ዶላር ያስወጣሉ።

የአየርላንድ ጦር ኃይሎች የቀድሞ አዛዥ ምክትል አድሚራል ማርክ ሜሌት ለቢቢሲ ቬሪፍይ እንደተናገሩት የሚሳዔል ጥቃት መከላከያዎቹ "እጅግ ውስብስብ" የሆነ ቀጣናዊ የመከላከያ ሥርዓት አካል በመሆናቸው "በፍጥነት ወይም በቀላሉ ሊተኩ የማይችሉ" ናቸው ብለዋል።

የኢራን ጥቃቶች በሳዑዲ አረቢያ በሚገኘው የልዑል ሱልጣን አየር ኃይል ሰፈር ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ አየር ላይ ነዳጅ በሚሞሉ እና የቅኝት አውሮፕላኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የሳተላይት ምሥሎችን የተነተኑ ባለሙያዎች ጠቁመዋል።

ውድመት የደረሰበት አንደኛው አውሮፕላን ኢ-3 ሴንትሪ የተባለ የቅኝት አውሮፕላን መሆኑን በተንታኞች ተለይቷል። ይህንን ወታደራዊ አውሮፕላን ለመተካት እስከ 700 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ እንደሚችል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የኢራን ጥቃት በሌሎች ቦታዎችም የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ አድርጓል። በኩዌት ውስጥ የሚገኙት የአሊ አል ሳሌም የ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön