'ቤተሰቦቼ ከሞትኩ በኋላ መርዶ ቢነገራቸው ይሻላል' - በሳዑዲ እስር ቤቶች የሞት ቅጣት የሚጠባበቁት ኢትዮጵያውያን
በሳዑዲ አረቢያ ሦስት ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ ክስ የሞት ፍርድ ሲፈጸምባቸው ቢያንስ 65 የሚሆኑት ደግሞ ፍርዳቸው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ጊዜ እየተጠባበቁ መሆኑን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የሳዑዲ መገናኛ ብዙኃን በካሃሚስ ሙሻይት ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርድ እየጠበቁ መሆኑን ዘግበዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እነዚህ ወጣቶች ከመርፈዱ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ይድረስልን ሲሉ ይማጸናሉ።
ከሃገሩ ለመሰደድ የተገደደውም በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሸሽቶ ነው።
"በ2013 ከትግራይ ምሥራቃዊ ዞን እገላ ከምትባለው ወረዳ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ስደት አቀና" ይላል በትግራይ የሚኖረው የአጎቱ ልጅ መብራህቶም አለማ።
የመን ውስጥ ጥቂት ወራትን አሳልፎ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሲደርስ ብዙም ሳይቆይ ተያዘ። በወቅቱ ቤተሰቡ ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየተሻገረ እንደሆነ የሚገልጹ መልዕክቶች ይደርሳቸው ነበር። በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ዘመዶች አማካኝነት ነበር ስላለበት ሁኔታ መረጃ የሚደርሳቸው።
የመን ውስጥ እያለ "ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስደርስ እደውላለሁ" ብሎ የነበረ ቢሆንም ከዛ በኋላ ግን ድምጹ ጠፋ። ረዥም ግዜ ከጠበቁ በኋላ እንደታሰረ ሰሙ። ከታሰረ ከ3 ዓመታት በላይ አልፎት ነበር።
"እስር ቤት ሆኖ በተለይ ስለ ቤተሰቡ ደኅንነት ይጠይቀኝ ነበር። በተለይ ታላቅ ወንድሙ እርሱን ተከትሎ ወደ ስደት አምርቶ የመን ከገባ በኋላ እስር ቤት ሆኖ ስለሱ ይጨነቅ ነበር" ሲል የአክስቱ ልጅ ተስፋይ ከሳዑዲ አረቢያ ለቢቢሲ ተናግሯል።
ወንድሙ ወደ የመን ሲገባ ክብሮም በእስር ቤት ሁለት ዓመታት አሳልፎ ነበር። ስደተኞች ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር በሚሰባሰቡበት ቦታ ወንድሙ በየመን ታጣቂዎች ተገድሏል። ክብሮም የወንድሙን ሞት በእስር ቤት ሲሰማ ጭንቀቱ በመራራ ሀዘንና ቁጭት ተተካ።
ክብሮም በሳዑዲ አረቢያ ከሚገኘውን የአጎቱን ልጅ ጋር ሲደዋወል "አሁን እዚያ ለሦስት ዓመታት ስለቆየን ሊፈቱን ይችላሉ። ቢያቆዩንም ራሱ ለአንድ ዓመት ነው" በማለት በተስፋ ይናገር ነበር።
የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት የነገራቸው በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለነበሩት አንዳንድ ጓደኞቹ እና እስር ቤት ውስጥ ላሉ ብቻ ነበር። ለቤተሰቦቹ ግን እንዳይጨናነቁ በማሰብ የእስር ግዜውን ጨርሶ እንደሚፈታ ነበር የሚነግራቸው።
"ተይዞ ሲታሰር እዚህ አገር ውስጥ ወላጆቹን እና ዘመዶቹ አናገኘውም። ነገር ግን በሳዑዲ አረቢያ ካሉ ሌሎች ዘመዶቻችን ጋር ይገናኝ ነበር። ስንጠይቃቸው 'እያገኘነው ነው፤ ይለቀቃል' ይሉን ነበር" ይላል የአጎቱ ልጅ መብራህቶም።
የሞት ፍርዱ ከመፈጸሙ ከሁለት ሳምንታት በፊት ሳዑዲ አረቢያ ወደሚገኘው የአክስቱ ልጅ ተስፋይ ደውሎ ለመጨረሻ ጊዜ ተነጋገሩ።
ሁልጊዜ እንደሚለው በአጭሩ "ደህና ነኝ" ካለ በኋላ እሱን ተከትለው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስለገቡት ሌሎች ታናናሽ ወንድሞቹ ሁኔታ መጠየቅ ጀመረ።
ያኔ በስልክ 'አደራ ተባበራቸው፤ ተከታተላቸው። ሥራ እንዲያገኙ አግዛቸው' እንዳለው ተስፋይ ይገልጻል።
"በተገደለበት ቀን ዋዜማ እዚህ ሳዑዲ አረቢያ ወደ ሚገኝው ሌላ የአጎቴ ልጅ ጋር ደውሎ ነበር። እየተጣደፈ ስለ ደኅንነታችን ብቻ ነበር የጠየቀው" የሚለው ተስፋይ ብዙም ሳያወሩ ስልኩን እንደዘጋው ለቢቢሲ ተናግሯል።
በማግስቱ ከሰዓት በኋላ በእስር ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች እስረኞች ወደ ተስፋይ ደወሉ። አሳዛኙን መርዶም ነገሯቸው።
የሳዑዲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሲር ዞን ውስጥ ሦስት ኢትዮጵያውያን በሞት ስለመቀጣታቸው ባወጣው መግለጫ ላይ የሃይማኖት መልዕክቶችን እና የሸሪዓ ሕግን በመጥቀስ የሟቾችን ስም ይዘረዝራል።
"ኪዳኔ አንገሶም ወልዳይ፣ ፊልሞን ሐጎስ ገብረመስቀል እና ክብሮም ገብረማርያም ገብረእግዚአብሔር ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ተሳትፈዋል" የሚለው መግለጫው፣ በምርመራ ውጤት መሠረት ወንጀሉን ፈጽመው እንደተከሰሱ ያመለክታል።
በእነርሱ ላይ የቀረበው ክስ ከተረጋገጠ በኋላ ሞት እንደተፈረደባቸው እና በሸሪዓ ሕግ መሠረት ፍርዱ ተፈጻሚ እንዲሆን መወሰኑን በመጥቀስ "የሞት ቅጣቱ ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም. በአሲር ዞን ተፈጻሚ ሆኗል" ይላል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ሁለት ታናናሾቹ እና በየመን የተገደለው የበኩር ልጅ ጨምሮ አራቱም ወንድማማቾች ወደ ስደት አቅንተው ሁለቱም በወጡበት የጠበቃቸው ሞት ነበር።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ወላጆችና ዘመዶች አንዳቸውም ልጆቻቸው ከመታሰራቸው በስተቀር የሞት ፍርድ እንደተፈረደባቸው አያውቁም።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ተስፋይ ወደ ክብሮም ወላጆች እየደወለ "ፍርዱ ቀላል ይሆናል፤ የረመዳን ጾም ሲገባ ምህረት ይደረግላቸዋል" ይላቸው ነበር።
ነገር ግን ፍርዳቸው ሲፈጸም የሦስቱም መርዶ በትግራይ ወደምትገኘው እገላ ወረዳ ደረሰ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሦስቱም ከዚያች ወረዳ የመጡ ናቸው። ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተሰደዱበት ጊዜ ግን የተለያየ ነው።
"መርዶው በተሰማ ጊዜ በእገላ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ተፈጠረ። ምክንያቱም ከአካባቢው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተሰደዱ ብዙ ወጣቶች አሉ።
"በተነገረን መሠረት 'ወደ ፍርድ ቤት ልንወስዳችሁ ነው' በሚል ነው ከእስር ቤት አውጥተው የገደሏቸው" ይ
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →