የአሜሪካ የኤርትራን ማዕቀቦች ማንሳት፡ ቀይ ባሕር የሸፈነው የሰብአዊ መብት ጥያቄ?
አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀቦች ለማንሳት ማቀዷ ሲሰማ ከጀርባ ያለው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ አጭሯል። ኤርትራ ላይ የሚቀርቡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶችን በተመለከተ ተጠያቂነት እና ፍትሕ ሳይሰፍን ማዕቀቦችን ማንሳት ምን ያስከትላል? ለምን አሁን ማዕቀቦችን ማንሳት አስፈለገ? ይህ የአሜሪካ ሐሳብ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምን ማለት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችም እየተነሱ ነው።
ሕገ መንግሥት እና ምክር ቤት አልባዋ፣ ምርጫ የማይካሄድባት፣ ነጻ መገናኛ ብዙኃን የከሰሙባት፣ ገለልተኛ የፍትሕ ሥርዓትም ያልገነባችው ኤርትራ በዓለማችን አምባገነን አገራት ዝርዝር ውስጥ በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱ አንዷ ሆና ቀጥላለች።
ከአሜሪካ በተጨማሪ የመንግሥታቱ ድርጅት እና የአውሮፓ ኅብረት የተለያዩ ማዕቀቦችን ጥለውባትም ቆይተዋል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ንግግር በሚያደርጉባቸው አጋጣሚዎች ምዕራባውያንን በተለይም አሜሪካን አጥብቀው ይተቻሉ።
አሜሪካ "ለሰብአዊ መብት እና ዴሞክራሲ መከበር" በሚል የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ልታነሳ እንደሆነ ተዘግቧል።
ሮይተርስ ባለፈው ሳምንት ያስነበበው ዘገባ፤ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት "ለማሻሻል እንደምትፈልግ" ይጠቁማል። ኤርትራም ይሄንን እንደምትደግፍ በይፋ አስታውቃለች።
አሜሪካ ማዕቀቦችን ከማንሳቷ ጀርባ ያለው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት ምንድን ነው? ኤርትራ ላይ የሚቀርቡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶችን በተመለከተ ተጠያቂነት እና ፍትሕ ሳይሰፍን ማዕቀቦችን ማንሳትስ ምን ያስከትላል? የሚሉት ጥያቄዎች ተነስተዋል።
የአብዛኞቹ ጥያቄዎች መነሻ ለምን አሁን ላይ ማዕቀቦችን ማንሳት አስፈለገ? የሚለው ሲሆን፤ በተያያዥም የኤርትራ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻሻል ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምን ማለት ነው? የሚለውን ማንሳት ይቻላል።
አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በወራት ውስጥ ዓለምን እያመሰቃቀለ ነው። የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የነዳጅ እና ሸቀጦች አቅርቦትን ጨምሮ ያልነካው ዘርፍ የለም።
ኢራን በኤደን ባሕረ ሰላጤ እና በቀይ ባሕር መካከል የሚገኘው የባብ-ኤል መንደብ ወሽመጥን ለመዝጋት መዛቷ ደግሞ ቀውሱን ያባብሳል።
በሌላ በኩል የኢራን ደጋፊ የሆኑት የየመን ሁቲ አማጺያን ለቀይ ባሕር ስጋት ሆነዋል። በባብ-ኤል መንዳብ አቅራቢያ መርከቦች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳዔሎች ጥቃቶች ፈጽመዋል።
በዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ አሜሪካ በቀይ ባሕር ላይ ኤርትራን "ስትራቴጂያዊ አጋር" ማድረግ እንደምትፈልግ የቀጣናው ፖለቲካ ተንታኞች ተናግረዋል።
ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሚነሳው ጥያቄ ደግሞ ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት የሰብአዊ መብት ጥያቄን ይበልጣል? የሚለው ነው።
በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩት ኤርትራዊት የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የሂውማን ራይትስ ኮንሰርን ኤርትራ ዳይሬክተር ኤልሳ ጭሮም "የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሳይሻሻል ግንኙነትን ማደስ፤ ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት ከፍትሕ እና ከሰብአዊ ክብር ይበልጣል የሚል አደገኛ መልዕክት ያስተላልፋል" ይላሉ።
የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሻ ባዲር በበኩላቸው፤ "የሰብአዊ መብት ጥሰትን ችላ ያለ የሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲ ለዓመታት የተፈጸሙ ሰፊ ጥሰቶች ያለ ቅጣት መታለፍን የሚያሰርጽ ነው" ብለዋል።
ከአራት ዓመታት በፊት በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ሥር የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኤርትራ ላይ ማዕቀቦች ሲጥል በትግራይ ጦርነት ከተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተገናኘ ነው።
ማዕቀቡ "ለቀውሱ እና ግጭቱ አስተዋጽኦ ያደረጉ ኤርትራውያንን" የሚመለከት እንደሆነ ተገልጿል። እነዚህ አካላት "የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ሉዓላዊነት በማወክም" ተከስሰዋል።
በአውሮፓውያኑ ታኅሣሥ 2021 የአሜሪካ መንግሥት በኤርትራ ገዢ ፓርቲ ሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ (ሕግዴፍ) እንዲሁም ከፓርቲው ጋር ትስስር ባላቸው ሕድሪ ትረስት እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ላይ ማዕቀብ ጥሏል።
የኤርትራ ገዢ ፓርቲ የምጣኔ ሃብት አማካሪ ሐጎስ ገብረሕይወት ወልደኪዳን፣ የኤርትራ ብሔራዊ ደኅንነት ኃላፊ ብርጋዴር ጄነራል አብርሃ ካሳ ነማርያም እና የኤርትራ ጦር ኃይል ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊልጶስ ወልደዮሐንስ ላይም ዕቀባ ተጥሏል።
የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት "በዝርፊያ፣ በወሲባዊ ጥቃት፣ ንጹኃንን በመግደል እና ሰብአዊ እርዳታን በማስተጓጎል" ተከስሰዋል።
የአሜሪካ መንግሥት የኤርትራ ኃይሎች እንዲሁም ገዢው ፓርቲው እና ባለሥልጣኖች "በጭፍጨፋ፣ በዘረፋ፣ በወሲባዊ ጥቃት እና የተኩስ አቁምን በማደናቀፍ" ተጠያቂ አድርጓል።
በኤርትራ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰው እንግልት፣ የነጻ መገናኛ ብዙኃን አፈና፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች የሚገጥማቸው ጫና እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የሁለቱን አገራት ግንኙነት እንዳሻከሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በድረ ገጹ አስፍሯል።
የኤርትራ መንግሥት የሚቀርቡበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ማሻሻል ሳያደርግ ማዕቀቦቹን ማንሳትን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →