የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመናቸው ማብቃቱን ተከትሎ የተፈጠረው አጣብቂኝ

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 15.05.2026
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመናቸው ማብቃቱን ተከትሎ የተፈጠረው አጣብቂኝ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ያደረጉትን ሙከራ ተከትሎ ከዚህ ቀደም አጋጥሟቸው አያውቅም የተባለ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተጋፈጡ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን የሚያበቃው አርብ ግንቦት 7/2018 ዓ.ም. ነው። ይህ ሁኔታም ሶማሊያን ቀውስ ውስጥ በማስገባት ለአልሻባብ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ያደረጉትን ሙከራ ተከትሎ ከዚህ ቀደም አጋጥሟቸው አያውቅም የተባለ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተጋፈጡ ነው።

በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን የሚያበቃው አርብ ግንቦት 7/2018 ዓ.ም. ነው።

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ የራሳቸውን እና የፓርላማውን ሥልጣን ከአራት ወደ አምስት ዓመት ለማራዘም እና እስከ ሚቀጥለው ዓመት ምርጫውን ለማራዘም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ለማድረግ ጥረት ካደረጉ በኋላ ውጥረት ጨምሯል።

ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቢያንሰ ሁለት ሰዎች ከተገደሉ እና በርካቶች ከተጎዱ በኋላ መንግሥት በአገሪቱ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ ግንቦት 3/2018 ዓ.ም. የድጋፍ ሠልፎችን አካሄዷል።

የደኅንነት ኃይሎች ተቃዋሚዎች ተጨማሪ ሠልፎች እንዳያካሄዱ ለመከላከል በመሪዎቻቸው መኖሪያ አካባቢ ተሰማርተዋል።

ዋነኛው የተቃዋሚ ጥምረት የሆነው እና የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼክ አህመድን እና በርካታ ጠቅላይ ሚኒስትሮችን፣ የፑንትላንድ እና የጁባላንድ ግዛት መሪዎችን የያዘው 'ሶማሊ ፊውቸር ካውንስል' ፕሬዝዳንቱ ሕገ መንግሥታዊ የሥልጣን ገደባቸው ካበቃ በኋላ ቅቡልነት አይኖራቸውም ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ፕሬዝዳንቱን ሥልጣንን ይጠቀልላሉ በማለት የሚወነጅሏቸው ሲሆን፣ ድርጊታቸው ወደ አዲስ አለመረጋጋት እና ግጭት እንደሚገፋት አስጠንቅቀዋል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ ሁሉም የፖለቲካ ባለድርሻ አካላት መካከል የአሁኑ ፕሬዝዳንት የሥልጣን ጊዜ ሳያበቃ አካታች የምርጫ ሂደት እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጋቢት ወር ፓርላማው የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን የሚያራዝም እና ምርጫን የሚያዘገይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎችን አጽድቋል። ይህ ግን በተቃዋሚ ቡድኖች ሰፊ ትችት እንዲቀሰቀስ አድርጓል።

የቀድሞው የደቡብ ምዕራብ ግዛት ፕሬዝዳንት አብዲያስ ላፍታጋሬ በፌደራል መንግሥቱ ወታደሮች ከተነሱ ከቀናት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የግዛቲቱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ሆነው ሲሾሙ ውጥረቱ የበለጠ ተባብሷል።

የፌደራል መንግሥቱ በደቡብ ምዕራብ ቀጥተኛ ምርጫ እንዲያካሄድ ያስተላለፈው ውሳኔ ጋር በተጣጣመ መልኩ በጋልሙዱግ እና ሒርሸበሌ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ በመወሰኑ በሞቃዲሹ እና በተቃዋሚ መሪዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል።

የሞሐሙድ ተቺዎች አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚለው ዕቅድ አለመረጋጋት፣ ውስን የሆነ የማዕከላዊ መንግሥት ቁጥጥር እንዲሁም ያልተፈቱ ሕገ መንግሥታዊ ግጭቶች ባሉበት ከአውሮፓውያኑ 2000 ጀምሮ በሥራ ላይ ያለውን በጎሳ ላይ የተመሠረተውን የምርጫ ሥርዓት ለመተው አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ ይከራከራሉ።

መንግሥት በሞቃዲሹ የያዘው የማፍረስ ዘመቻ ተቃዋሚዎች "የሕዝብ መሬትን ለግል ፍላጎት እየቸበቸቡ ነው" በማለታቸው ውጥረትን ካባባሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኗል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋና ከተማዋ የጋዜጠኞች እና የአክቲቪስቶች መታሰር በአገሪቱ እያደገ የመጣውን የሚዲያ ዕቀባ እና የፖለቲካ አለመግባባት እንዲያድግ አድርጓል።

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በአሜሪካ አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥቱ እና በተቃዋሚዎች መካከል ግንቦት 5/2018 ዓ.ም. የተደረገውን ውይይት ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።

የመንግሥት ልዑካን በፕሬዝዳንት ሞሐሙድ እና ቀዳማይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳላህ አህመድ ጃማን የተወከለ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ደግሞ የተወከሉት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼክ አህመድ እና በፑንትላንድ መሪ ሳኢድ አብዱላሂ ዴኒ ነው።

በግል ባለቤትነት የተያዘው ሶማሊ ጋርዲያን ድረ ገጽ ዳግም የሚቀሰቀስ አለመረጋጋት ለዓመታት የተደረገውን አገር የመገንባት ጥረት እንዳይቀለብሰው አስጠንቅቋል።

ድረገጹ የተቃዋሚዎች የመጀመሪያ ጥያቄ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ደጋፊዎቻቸው እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ነው ሲል ዘግቧል።

የቀድሞው ሚኒስትር አብዲርሃማን ባድዮው "ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ጣልቃ የገቡት ዘግይተው በመሆኑ በሁለቱም ወገን ላይ የሚያደርጉት ጫና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም" ብለዋል።

ሙስታቅባል የተባለ ሌላ የግል መገናኛ ብዙኃን ደግሞ ሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች በምርጫ እና ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያዎች ላይ ባለመስማማታቸው ግንቦት 6 ድርድራቸው ይቀጥላል ብሎ ነበር።

ጋሮዌ ኦንላየን በበኩሉ ስማቸውን ያተገለጸ ምንጮች ጠቅሶ የፌደራል መንግሥቱ ቴክኒካል ኮሚቴ እንዲቋቋም እየገፉ ነው ሲል ዘግቧል።

ተቃዋሚዎች ግን ይህንን ዕቅድ ውድቅ አድርገው "የግንቦት 7 ቀነ ገደብ ለማለፍ የመጣ ብልሃት ነው" ሲሉ መተቸታቸውን ዘግቧል።

የአልሸባብ ደጋፊ የሆነው አል ፉርቃን በበኩሉ "በመንግሥት እና በተቃዋሚዎች መካከል ያለ አለመተማመንን" አጉ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön