ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት የፈጠረችበት ርካሹ ድሮን

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 11.03.2026
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት የፈጠረችበት ርካሹ ድሮን

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ኢራን እየተፈጸመባት ላለው ጥቃት አጸፋውን በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ እየፈጸመች ነው። ለዚህ ደግሞ ኢራን ርካሽ እና ውጤታማ የሆኑትን ሻሂድ-136 የተባሉ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመች ነው። ይህ በምሥል እና በቪዲዮ የተደገፈው ዘገባ ስለድሮኖቹ ምንነት ይተነትናል።

ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ጥቃትን ስትጀምር የአገሪቱን የሚሳዔሎች እና የሚሳዔል ኢንዱስትሪ "ሙሉ በሙሉ ይደመሰሳል" ብለዋል። ነገር ግን ስለ ኢራን ድሮኖች ያሉት ነገር አልነበረም።

ጦርነቱ ከተጀመረ ሳምንት ያለፈው ሲሆን፣ ኢራን የአገራትን የአየር መከላከያን ለማጨናነቅ እና በቀጣናው ትርምስ ለመፍጠር በማሰብ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ዒላማዎች ላይ ከሁለት ሺህ በላይ ርካሽ ድሮኖችን አስወንጭፋለች።

እነዚህ አጥፍቶ ጠፊ (ካሚካዚ) ሻሄድ ድሮኖች ከዒላማቸው ጋር በሚጋጩበት ጊዜ የሚፈነዱ ፈንጂዎችን ይዘው ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። እስካሁን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ እጅግ የከፋው ጉዳት የደረሰው አንድ ድሮን በኩዌት የሚገኝ ጦር ሰፈርን መትቶ ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች በመገደላቸው ነው።

አብዛኞቹ ጥቃቶች የተፈጸሙት በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች ላይ ሲሆን፣ ሁሉም የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባላት እና መሳሪያዎችን በተወሰነ ደረጃ የሚያስተናግዱ ናቸው።

በተጨማሪም ኢምባሲዎችን፣ ቁልፍ የኃይል መሠረተ ልማቶችን፣ የንግድ አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና ቅንጡ ሆቴሎችን ዒላማ አድርገዋል።

አንዳንድ ጥቃቶች በተጨናነቁ ከተሞች ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ይህም በጎዳናዎች እና በባሕረ ሰላጤው አገራት መንግሥታት ላይም ስጋት ፈጥሯል። አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ይህ “ሽብር ለመፍጠር” እና ግጭቱን በቶሎ እንዲቆም በአሜሪካ ላይ ጫና ለመፍጠር የኢራን ስትራቴጂ አካል ሊሆን ይችላል።

ትክክለኛነቱ በቢቢሲ የተረጋገጠ አንድ ቪዲዮ የኢራን ድሮን በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ የባሕር ኃይል አምስተኛ ምድብ ዋና መሥሪያ ቤት ወዳለ ራዳር ሚመስል ነገር በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች ተምዘግዝጎ ሲመታ ፍርስራሹ በአየር ላይ ሲበተን እና መዋቅሩ ሲፈርስ ያሳያል።

ሌላ ቪዲዮ ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚገኘው ሰው ሠራሽ ደሴት ላይ ከሚገኝ ሆቴል ጋር ሲጋጭ በከተዋ ውስጥ ንዝረትን እና ግዙፍ የእሳት ኳስ የፈጠረ ከባድ ፍንዳታ ሲፈጥር አሳይቷል።

የድሮን ጥቃት በተለይ በቀጣናው የነዳጅ ማምረቻ ዘርፍ ላይ ያደረሰው ተፅእኖ የጎላ ነው። በባሕረ ሰላጤው ዳርቻ ራስ ታኑራ ውስጥ የሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የእሳት ቃጠሎ በመነሳቱ ምርት አቁሟል።

በዓለም ትልቁ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ማዕከል የሆነው የኳታር ተቋም የኢራን ድሮኖች ጥቃት ዒላማ በመሆኑ ምክንያት ተዘግቷል።

ድሮኖች ባላቸው ቀላል ዲዛይን እና ለማምረት በአንጻራዊነት ርካሽ በመሆናቸው በስፋት ጥቅም ላይ ውለው በቀጣናው ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው። በኢራን የሚመረተው ረዥም ርቀት በመጓዝ ዒላማውን መምታት የሚችለው ሻሂድ 136 ድሮን ከ20,000 እስከ 50,000 ዶላር የሚያስወጣ ነው።

ልዩ የሆነው የሻሂድ ከፍተኛ የንዝረት ድምጽ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በቀጣናው በስልኮች በተቀረጹ ቪዲዮዎች ላይ ተሰምቷል። አስገራሚው ድምጽ ከታች ባለው ቪዲዮ ላይ በግልፅ ይሰማል፣ ይህም አንድ ድሮን በባህሬን ዋና ከተማ ማናና ቅዳሜ እና እሁድ አንድ ሕንጻን ሲመታ ያሳያል።

ከብዙ ተራ ድሮኖች በተለየ ሻሂድ ድሮን በአየር ላይ እያለ በርቀት መቆጣጠሪያ የሚሠራ አይደለም። ይልቁንም የሳተላይት ቅኝት አንቴና ዘዴን በመጠቀም ወደ ሚመታው ዒላማ የተቀመጠለትን መንገድ ለመከተል እንዲችል አስቀድሞ ፕሮግራም ይደረጋል። በዚህም ሲነሳ የታለመለትን መንገድ ተከትሎ ወደ ሚመታው ዒላማ በቀጥታ ያቀናል። ድሮኑ 2500 ኪሜ ርቀት መጓዝ የሚችል ሲሆን፣ ከቴህራን ተነስቶ እስከ ግሪክ አቴንስ መብረር ይችላል።

በተለይ ከባላስቲክ ሚሳዔሎች ጋር ሲነጻጸር ፈጣን ባይሆንም፤ ድሮኑ ባለው አነስ ያለ መጠን እና በዝቅተኛ ከፍታ ላይ በመብረር በሚሳዔል ላይ በሚያተኩሩ ራዳሮች እንዲሁም በሌሎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ሳይታይ ማለፍ ይችላል።

ሻሄድ ድሮኖች በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ብዙ ሕዝብ በሚበዛባቸው ከተሞች እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሩሲያ ተጠቅማባቸዋለች። ኢራን ሻሂድ ድሮኖችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለአጋሯ ሩሲያ ሰጥታለች፤ አሁን ደግሞ ሩሲያ በኢራን ዲዛይን ላይ በመመሥረት የራሷን ድሮን እያመረተች ነው።

የቀድሞ የአሜሪካ የባሕር ኃይል፣ የሲአይኤ ወታደራዊ መኮንን እና የመካከለኛው ምሥራቅ መከላከያ የተባለው ተቋም ምክትል ረዳት ፀሐፊ የሆኑት ሚክ ሙልሮይ ድሮኖቹ ቀደም ሲል በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ “በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ መሆናቸውን” በማረጋገጥ፣ አሜሪካም የራሷን ዓይነት መሥራቷን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሉካስ ተብሎ የሚታወቀው በዝቅተኛ ወጪ የተሠራ እና ያለአንቀሳቃሽ የሚበር የጥቃት ድሮንን አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ባ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön