አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በፈጸመችባቸው አገራት ምን ተከሰተ?

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 23.03.2026
አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በፈጸመችባቸው አገራት ምን ተከሰተ?

ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ጦርነት ተመልሳለች። ዋሽንግተን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቀጣናው በተካሄዱ ጦርነቶች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተሳተፈች ሲሆን፣ ሁሉም ያመጡት ውጤት ላይ በአንድ ድምጽ ከስምምነት መድረስ አይቻልም። በተለይ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ያደረገቻቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ምን ውጤት አስገኙ?

ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ጦርነት ተመልሳለች። ዋሽንግተን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቀጣናው በተካሄዱ ጦርነቶች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተሳተፈች ሲሆን፣ ሁሉም ያመጡት ውጤት ላይ በአንድ ድምጽ ከስምምነት መድረስ አይቻልም።

አሁን አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በጥምረት በመሆን በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት የተጀመረው ጦርነት የአገሪቱን ከፍተኛ መሪ አሊ ኻሜኒን ገድሏል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን መሪ በማስወገድ፣ የአገሪቱን የኒውክሌር ፕሮግራም ማስቆም እንዲሁም የሥርዓት ለውጥ ማምጣት ፍላጎታቸው ነው።

ትራምፕ በቀጣናው ውስጥ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የፈጸሙ የአሜሪካ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አይደሉም።

አባት እና ልጁ ጆርጅ ቡሽ እንዲሁም ባራክ ኦባማ ቀደም ሲል በኢራቅ ከሳዳም ሁሴን ጋር ወይም በሊቢያ ከሙአመር ጋዳፊ ጋር ጦርነት ገጥመው ነበር።

የእነዚህ መሪዎች ከሥልጣን መወገድ ለአገራቱ ዲሞክራሲንም ሆነ የናፈቁትን ነጻነት አላስገኘም። ከዚያ ይልቅ በአገራቱ ውስጥ እስካሁን የዘለቀ የእርስ በርስ ጦርነት እና አለመረጋጋት ፈጥሯል።

በሶሪያ አሜሪካ እስላማዊ መንግሥት በማለት የምትጠራውን ቡድን ለማስወገድ ድጋፍ ያደረገች ቢሆንም በ2024 አል አሳድ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ሌሎች እስላማዊ ቡድኖች ሥልጣን ተቆጣጥረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍጋኒስታን፣ የታሊባን አገዛዝ አሜሪካ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በአገሪቱ ውስጥ ጣልቃ ከገባች በኋላ በ2021 ወደ ሥልጣን ተመልሷል።

በኦባማ አስተዳደር ወቅት ዲፕሎማት እና የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የነበሩት ፊሊፕ ጎርደን በአውሮፓውያኑ 2015 ባወጡት ጽሑፍ አገራቸው በቀጣናው ውስጥ ያደረገቻቸው ጣልቃ ገብነቶች ቀውስ ማስከተላቸውን አስፍረዋል።

"በኢራቅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ጣልቃ ገብታ አገሪቱን ተቆጣጠረች፤ ውጤቱም እጅግ ውድ ዋጋ ያስከፈለ ነበር። በሊቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ጣልቃ ገብታ አገሪቱን አልተቆጣጠረችም፣ ውጤቱም እዚህም የከፋ ነበር። በሶሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ጣልቃ አልገባችም ወይም አገሪቱን አልተቆጣጠረችም ውጤቱ ደግሞ ከባድ ነበር።"

ባለሙያዎች እንደሚሉት የአሜሪካ በአገራት ውስጥ ጣልቃ መግባት ለራሷ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ቀጣናውን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ ነበር።

በካይሮ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ፕሮፌሰር ኢብራሂም አዋድ "በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት በአብዛኛው የሚከሰተው ከውጭ በሚኖር ጣልቃ ገብነት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ሙንዶ ያስረዳሉ።

ምንም እንኳን ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ ወይም የመን ከባድ የአስተዳደር ችግሮች የሰፈነባቸው ወይም አምባገነን ሥርዓቶች ያሏቸው አገራት ቢሆኑም፣ እነዚህ ጉዳዮች በአዋድ አስተያየት "በውጭ ጣልቃ ገብነት ሊፈቱ የሚችሉ" አልነበሩም።

ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ በርካታ አገራት ውስጥ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ፈጽማለች። አንዳንድ ጊዜ የጦርነቱ ዋነኛ ተሳታፊ በሌሎች ጊዜያት ደግሞ ደጋፊ ሚና በመያዝ ወይም የሰፊ ጥምረት አካል የሆነችበት ጊዜያት አሉ።

ለመሆኑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አሜሪካ በየትኞቹ አገራት ውስጥ የወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ፈጽማ ምን ተከሰተ?

ኢራቅ በሳዳም ሁሴን አመራር ስር ሳለች በአውሮፓውያኑ 1990 የኩዌት የነዳጅ ዘይትን ለመቆጣጠር እና ቀጣናዊ የበላይነቷን ለማጠናከር ወረራ ፈጽመለች።

በዋሽንግተን የሚመራ እና በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፍ ወታደራዊ ጥምረት "ኦፕሬሽን ዴዘርት ስቶርም" [ዘመቻ የበረሃው ማዕበል] የተባለ ዘመቻ አካሂዶ ኩዌትን ታድጋታለች።

ጥምረቱ በከፍተኛ የአየር ድብደባዎች እና ፈጣን በሆነ የእግረኛ ወታደሮች ስምሪት የታገዘ ነበር። ይህ ዘመቻ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኢራቅ ጦርን በማስወጣት ኩዌትን ነፃ ማውጣት ችሏል።

በወቅቱ ሳዳም ሁሴን ማዕቀብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ በአገር ውስጥም አለመረጋጋት እንዲቀሰቀስ እና የጎሳ ውጥረትን እንዲባባስ አድርጎ ነበር።

ይህ ዘመቻ በብዙዎች ዘንድ ዓለም አቀፍ ሕግን ወደነበረበት የመለሰ ወታደራዊ ስኬት ተደርጎ ተቆጥሮ ነበር።

ከበርሊን ግንብ መፍረስ እና ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ የተካሄደው ይህ የባሕረ ሰላጤው ጦርነት የአሜሪካን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አዲስ ዘመን ተደርጎ ተቆጠረ።

በአውሮፓውያኑ 2003፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በዩናይትድ ኪንግደም የሚመራ ሌላ ጥምረት፣ አገዛዙ የጅምላ እልቂት መሳሪያዎች መታጠቁን እና ከዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ጋር ግንኙነት እንዳለው በመግለጽ ኢራቅን ወረረ።

ኢራቅ አላት የተባሉት የጦር መሳሪያዎች ባይገኙም፤ ጥምረቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ባግዳድ ደርሶ ሳዳም ሁሴንን በቁጥጥር ስር በማዋል

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön