አሜሪካ እና እስራኤል ብዙዎቹን የኢራን መሪዎችን ገድለዋል፤ ትራምፕ ከማን ጋር ሊደራደሩ ይችላሉ?

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 26.03.2026
አሜሪካ እና እስራኤል ብዙዎቹን የኢራን መሪዎችን ገድለዋል፤ ትራምፕ ከማን ጋር ሊደራደሩ ይችላሉ?

አንድ ወር ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ከሞላ ጎደል አብዛኞቹ የኢራን ቁልፍ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች ተገድለዋል። ነገር ግን ኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር የምታደርገውን ፍልሚያ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ቀጥላለች። ከከባድ ውድመት እና የመሪዎቿ ግድያ በኋላ ኢራን በእነማን እየተመራች ነው?

የእስራኤል ጦር ያለምንም ተጨማሪ ፈቃድ የትኛውንም የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ዒላማ እንዲያደረግ መታዘዙን የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ተናግረዋል።

ይህንን ያሉት ጦሩ የቴህራን የደኅንነት እና የስለላ ሚኒስቴሮችን፤ አሊ ላሪጃኒ እና እስማኤል ኻቲብን መግደሉን ይፋ ካደረገ በኋላ ነው።

ካትዝ "ጠቅላየ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና እኔ ጦሩ ለደኅንነት እና ለውሳኔ ሰጪ አካል ቅርብ የሆነን የኢራን ባለሥልጣን ያለምንም ተጨማሪ ፈቃድ እንዲያስወግድ ፈቃድ ሰጥተናል" ብለዋል።

ነገር ግን እነዚህ ባለሥልጣናት በኢራን የሥልጣን ተዋረድ ውስጥ ምን ያሀል ወሳኝ ሚና ነበራቸው? አሁን አገሪቱን በበላይነት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው?

አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በከፈቱበት የመጀመሪያው ቀን የጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደል ብዙዎችን ያስደነገጠ ሆኗል።

የ86 ዓመቱ አዛውንት እአአ በ1979 የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክን የመሠረቱትን አያቶላህ ሩሆላህ ኾሜኒን ከተኩ በኋላ ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል አገሪቱን መርተዋል።

ኻሜኒ የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ እና የጦር ኃይሎች እንዲሁም የአብዮታዊ ዘቡ ዋና አዛዥ በመሆን በኢራን ውስጥ ከፍተኛውን ሥልጣን ነበር።

ምንም እንኳን ማንኛውንም ፖሊሲ ​ውድቅ ማድረግ እና ባለሥልጣንን በፈቃዳቸው መሾም ቢችሉም አምባገነን የሚባሉ መሪ አልነበሩም።

እጅግ ውስብስብ እና ተፎካካሪ በሆኑ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በመሆን አገሪቱን የመሩት አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፤ በኢራን ለውጥ ፈላጊዎች እና በወግ አጥባቂዎች መካከል ባለ ውዝግብ መካከል ተረጋግተው አገሪቱን መርተዋል።

ነገር ግን ኻሜኒ የተቃውሞ ድምጾች እንዲሰሙ ወይም ውድቅ ያደረጓቸው ፖሊሲዎች እንዲረቀቁ አልፎ አልፎ ይፈቅዳሉ።

ሞጅታባ ኻሜኒ አባታቸውን ተክተው ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በሕዝብ ታይተው፣ በቪዲዮ ተቀርጸው ወይም ፎቶግራፍ ተነስተው አያውቁም።

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ አዲሱ ጠቅላይ መሪ ቴህራን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ወላጆቻቸው እና ወንድማቸው በተገደሉበት ወቅት "ቆስለዋል ምናልባትም አካላቸው ጎድሏል" ብለዋል።

ሞጅታባ ጠቅላይ መሪ ከሆኑ በኋላ በመንግሥት ቴሌቪዥን ላይ በተነበበው የመጀመሪያ መግለጫቸው የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት በጦርነቱ የተገደሉ ዜጎቻቸውን ደም "እንደሚበቀሉ" ዝተዋል።

የፎቶው ባለመብት, COURTNEY BONNEAU/Middle East Images/AFP via Getty Images

አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት ጥቃት ከልጃቸው ጋር የተገደሉት የ68 ዓመቱ አሊ ላሪጃኒ ከኻሜኒ ሞት በኋላ ከተገደሉ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን መካከል አንዱ ናቸው።

የቀድሞ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ እአአ በ2004 ለኻሜኒ የደኅንነት አማካሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ለአስር ዓመታት ያገለገሉት የኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ ብሮድካስት ኃላፊ በመሆን ነው።

ነገር ግን በወቅቱ ከፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድ ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ከሥልጣናቸው ተነስተዋል።

ለ12 ዓመታት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ይህም ከየትኛውም ተሿሚ በላይ በኃላፊነቱ ላይ የቆዩ ያደርጋቸዋል።

ላሪጃኒ በጠቅላይ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ውስጥ ኻሜኒን የሚወክሉ ሲሆን፣ በታኅሣሥ እና ጥር በኢራን በተካሄደው ተቃውሞ ላይ የባሲጅ ሚሊሻ ኃይሎችን ጨምሮ ተቀቃዋሚ ሠልፈኞች ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ጠንካራ እርምጃ መውሰዳቸው በስፋት ይገለጻል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በእነዚህ የተቃውሞ ሠልፎች ቢያንስ 6,508 ሰዎች ሲገደሉ 53,000 ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የኢራን የደኅንነት እና የኒውክሌር ፖሊሲ አውጪ ቁልፍ ሰው እና ብቸኛው የኢራን ሪር አድሚራል የነበሩት የኻሜኒ የቅርብ አማካሪ አሊ ሻምኻኒ የካቲት 21 በቴህራን ላይ በተፈፀመው ጥቃት ተገድለዋል።

ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር ለ12 ቀናት በእስራኤልእና በኢራን መካከል በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቤታቸው ላይ ከተፈፀመው ጥቃት በሕይወት ተርፈዋል።

በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ በኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት ሻምኻኒ ከአብዮታዊ ዘብ አዛዦች መካከል አንዱ ነበሩ።

ከእነዚህም መካከል የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ሚኒስትር፣ የመከላከያ ሚኒስትር፣ የባሕር ኃይል አዛዥ እና የጠቅላይ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በአገሪቱ የተካሄዱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን በማፈን ረገድ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።

ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ፓክፑርም በየካቲት 21 በቴህራን ላይ በተፈፀመው ጥቃት መገደላቸውን የኢራን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ለ16 ዓመታት የአብዮታዊ ዘብ የምድር ጦር አ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön