አሜሪካ እና እስራኤል፤ በኢራን ላይ ምን ዓይነት ሳይበር ጥቃቶች ፈጸሙ? ኢራንስ?
ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም ኃይልን የተመለከቱ ውይይቶች በሚነሱባቸው ወቅቶች አሜሪካ እና እስራኤል እንዴት ኢራንን እያጠቁ እንደሆነ በምሥል ጭምር ከማሳየት ወደ ኋላ አይሉም። በባለሙያ የተዘጋጁ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎችን የሚጠቀመው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ፤ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የመሣሪያ፣ የጄት እና የመርከብ ዓይነቶችን የሚያሳዩ ልጥፎችን በየአጭር ሰዓት ልዩነት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይለጥፋል።
ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም ኃይልን የተመለከቱ ውይይቶች በሚነሱባቸው ወቅቶች አሜሪካ እና እስራኤል እንዴት ኢራንን እያጠቁ እንደሆነ በምሥል ጭምር ከማሳየት ወደ ኋላ አይሉም።
በባለሙያ የተዘጋጁ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎችን የሚጠቀመው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ፤ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የመሣሪያ፣ የጄት እና የመርከብ ዓይነቶችን የሚያሳዩ ልጥፎችን በየአጭር ሰዓት ልዩነት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይለጥፋል።
አሜሪካ እና እስራኤል በበይነ መረብ (ሳይበር) ምኅዳሩ ላይ እየተካሄደ ያለውን ነገር ለማሳየት ግን ይህንን ያህል ፍላጎት ያላቸው አይመስልም።
ለሰዓታት በሚቆዩት ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ በባለሥልጣናት ንግግሮች እንዲሁም በበርካታዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፎች ላይ የሳይበር ዘመቻን የተመለከተ ገለጻ የለም ማለት ይቻላል።
ኢራናውያን የሳይበር መንታፊዎች (ሀከሮች) ግን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ኩባንያ ላይ የሳይበር ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለው 'ስትራይከር' የተባለ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደጠቆሙት፤ በዚህ ጦርነት ውስጥ የሳይበር ጥቃት ከፍተኛ ሚና አለው።
"ከባሕር ወለል እስከ ጠፈር እና የሳይበር ምኅዳር፤ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸማችንን እንቀጥላለን" ሲሉ ተናግረዋል።
በጦርነቱ ውስጥ ምን ዓይነት የሳይበር ዘመቻዎች እየተካሄዱ ስለመሆኑ የምናውቀው እንዲሁም ዘመቻዎቹ ስለ ዘመናዊ ውጊያ ምን እንደሚነግሩን በዚህ ዘገባ ቀርቧል።
የፔንታጎን የጋራ ወታደራዊ አዛዦች ሊቀ መንበር የሆኑት ጄነራል ዳን ኬን፤ የጦርነቱ አካሄድ በተመለከተ ለወራት፤ አንዳንድ ጉዳዮች ላይም ለዓመታት ዕቅድ ሲዘጋጅለት እንደነበር ተናግረዋል።
ጥቃት የሚፈጸምባቸውን "የዒላማዎች ስብስብ" መለየት የዕቅዱ አካል እንደነበረም ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አብራርተዋል።
የጥቃት ዕቅድ ከመዘጋጀቱ አስቀድሞ የአሜሪካ እና የእስራኤል የሳይበር መንታፊዎች ወሳኝ ወደሆኑ የኢራን የኮምፒውተር ኔትዎርኮች ውስጥ ሰርገው ገብተው ሊሆን ይችላል።
ከአየር መከላከያ እና ወታደራዊ ኮሚዩኒኬሽን ጀርባ ያሉ የኮምፒውተር ኔትዎርኮች የሳይበር መንታፊዎች ዋነኛ ዒላማ መሆናቸው አይቀሬ ነው።
የብሪታኒያው ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፤ እስራኤል ግዙፍ የክትትል መረብ ለመገንባት እንዲያስችላት በኢራን ጎዳናዎች የሚገኙ የደኅንነት እና የትራፊክ ካሜራዎችን ጠልፋ ነበር።
በእነዚህ ካሜራዎች አማካኝነት ኋላ ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ እና ወታደራዊ አዛዦቻቸው "የዘውትር የውሎ ልምድ" ምን እንደሚመስል እንደተጠና በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ካሜራዎች "በአነስተኛ ወጪ የመንገዶች፣ የተቋማት እና የእንቅስቃሴዎችን ሁኔታ የተመለከተ የትክክለኛ ጊዜ መረጃ ስለሚያስገኙ" በሳይበር ውጊያ ውስጥ ዒላማ እየሆኑ መምጣታቸውን 'ቼክ ፖይንት' የተሰኘው የሳይበር ደኅንነት ኩባንያ የስጋት ስለላ ባለሙያ የሆኑት ሰርጌ ሻይኬቪች ያስረዳሉ።
ይህ ዓይነቱ መረጃ ሰላዮችን እንደማሰማራት ባሉ መደበኛ የስለላ ተግባራት ከሚገኘው መረጃ ጋር ተዳምሮ ጥቅም ላይ እንደሚውል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በእስራኤል ጦር የሳይበር መከላከል ባለሙያ የነበሩት ታል ኮሌንደር በበኩላቸው፤ "ብዙውን ጊዜ የሳይበር ዓለም ባለቤትነቱ የእኛ የሆነ ወሳኝ መሣሪያ አይደለም። የመረጃ ከባቢውን ለመቅረጽ የሚደግፍ እና በምድር ላይ ለሚከናወኑ ዘመቻዎችን የሚያግዝ አቅም መጨመሪያ መሣሪያ ነው" ይላሉ።
ኢራን ላይ የመጀመሪያዎቹ ጥቃቶች ከተፈጸሙ በኋላ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጄነራል ኬን፤ የአሜሪካ የሳይበር እና የጠፈር ዕዞችን "የመጀመሪያዎቹ እርምጃ ፈጻሚዎች" ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
እነዚህም "የኢራንን የመመልከት፣ ግንኙነት የማድረግ እና ምላሽ የመስጠት አቅሞችን እንደገደቡ" እና እንዳስተጓጎሉም በማንሳትም አሞካሽተዋቸዋል።
ለምሳሌ፤ የአያቶላህ ኻሜኒ የደኅንነት ቡድን ወደ ስፍራው እየመጣ ያለን ተዋጊ ጄት በተመለከተ ማስጠንቀቂያ እንዳይደርሰው ሲባል የሞባይል ስልክ ማማዎች እንዲጠለፉ ወይም እንዲጠፉ ተደርገው ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይጠቁማሉ።
ይህ ዓይነቱ ድርጊት ስለመፈጸሙ ማረጋገጫ አልተገኘም። ነገር ግን እንደ የዩክሬን ጦርነት ባሉ የተለያዩ ግጭቶች ውስጥ መሰል እርምጃዎች ተወስደው ተመልክተናል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴትም በቅርቡ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢራን ጦር አባላት "መቀናጀት እና ቀጣይነት ያለው ጥቃት መፈጸም ቀርቶ መነጋገር ወይም ግንኙነት መፍጠር አይችሉም ነበር" በማለት በ
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →