ኢትዮጵያ ለምን እስካሁን 'በጅብ ሃብቷ' አልተጠቀመችም?
በተለምዶ የጅቦች ስም የሚነሳው ከክፉ ነገር ጋር ተያይዞ ነው። ጅቦችን ማጉረስ ባህል ከሆነበት የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ውጭ ስለ ጅቦች ያለው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። በመቀለ ዩኒቨርስቲ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው የሼፊልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ግደይ ይርጋ ግን የተለየ ዕይታ አላቸው። ጅቦች የካንበን ልቀትን ይቀንሳሉ፤ አካባቢን በማጽዳት ከበሽታ ይከላከላሉ፤ ገንዘብም ይቆጥባሉ ቢባል ብዙዎች ያምኑ ይሆን?
በተለምዶ የጅቦች ስም የሚነሳው ከክፉ ነገር ጋር ተያይዞ ነው። ጅቦችን ማጉረስ ባህል ከሆነበት የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ውጭ ስለ ጅቦች ያለው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል።
በመቀለ ዩኒቨርስቲ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው የሼፊልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ግደይ ይርጋ ግን የተለየ ዕይታ አላቸው።
ጅቦችን በተመለከተ የሠሩት ጥናት እንሰሳቱ የአካባቢ ጥበቃን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳላቸው ይጠቁማል።
ጅቦች የካርበን ልቀትን ይቀንሳሉ፤ አካባቢን በማጽዳት ከበሽታ ይከላከላሉ፤ ገንዘብም ይቆጥባሉ ቢባል ብዙዎች ያምኑ ይሆን?
የአየር ንብረት ለውጥ ዓለምን እንቅልፍ ነስቷል። በአንድ ጽንፍ ከፍተኛ ወበቅ በሌላ ጽንፍ የጎርፍ መጥለቅለቅ ማስከተሉን ቀጥሏል።
የአየር ንብረት ለውጥን ከሚያባብሱ መካከል የካርበን ልቀት ይጠቀሳል። ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ሜቴንን ጨምሮ ሌሎችም የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ሲደማመር የካርበን ልቀት ይባላል።
በኢትዮጵያ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ ወይም ሌሎች እንሰሳት ከታረዱ በኋላ በየመንገዱ ቅሪታቸው ይጣላል።
ዶ/ር ግደይ እንደሚሉት፤ ይሄ የእንሰሳቱ ቅሪት ሲበሰብስ እንደ ሜቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ያለውን ግሪንሀውስ ጋዝ ይለቃል።
ጅቦች የእንሰሳት ቅሪተ አካል ከመበስበሱ በፊት ስለሚመገቡት የካርበን ልቀትን ይቀንሳሉ ማለት ነው።
"ጅቦች የእንሰሳት ቅሪተ አካል ሳይበሰብስ (decompose ሳያደርግ) በፊት ቶሎ ስለሚበሉት ጋዙ እንዳይለቅ ያደርጋሉ" ይላሉ።
ዶ/ር ግደይ ጥናታቸውን የሠሩት በመቀለ ከተማ ነው። ነገር ግን የጥናቱ ውጤት በሌሎች ከተሞችም ሊተገበር ይችላል።
እንደ ማሳያ መቀለን እንውሰድ። በመቀለ ከተማ ብቻ ጅቦች እና ሌሎችም ጥንብ አንሳዎች (scavengers) በየዓመቱ 1,063 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የካርበን ልቀትን ያስወግዳሉ።
ይህም አካባቢን በመጠበቅ ረገድ ጅቦች "ያልተጠበቀ ሚና እንዲኖራቸው" ማድረጉን አጥኚው ይናገራሉ።
በመቀለ ብቻ የዓመቱ የሚታረዱት እንሰሳት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ። ሁለት ሦስተኛው የእንሰሳቱ ቅሪት በየመንገዱ ይጣላል።
የቆሻሻ አወጋገድ የብዙ ከተሞች ችግር ነው። ዶ/ር ግደይ ጥናታቸውን በሠሩበት መቀለም የቆሻሻ አወጋገድ ሒደት "ደካማ" መሆኑን ይናገራሉ።
"ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት 40% ቆሻሻ ብቻ ነው የሚሰበሰበው" ይላሉ። ስለዚህም ቆሻሻ በየአካባቢው ተከምሮ ማየት የተለመደ ነው።
ጅቦች ቆሻሻን በመመገብ ከተሞችን ንጹህ የማድረግ ሚና ይጫወታሉ። በየዓመቱ 4,455 ሜትሪክ ቶን ቆሻሻ (organic waste) እንደሚያስወግዱ ጥናቱ ያሳያል።
ጅቦችን ተፈጥሯዊ ቆሻሻ ሰብሳቢ ልንላቸው እንችላለን። ጥናቱ እንደሚያሳየው፤ በዓመት ውስጥ መቀለ ቆሻሻ ለመሰብሰብ ወይም ለማስወገድ ታወጣ የነበረውን 89,000 ዶላር መቆጠብ ይቻላል።
ጅቦች መሰብሰብ እና መጓጓዝ ያለበትን ቆሻሻ መጠን ይቀንሳሉ። የከተማ ተፈጥሯዊ አጽጂዎች የሚባሉትም ለዚህ ነው።
የእንሰሳት ቅሪት በየቦታው ሲጣል ዝንብ፣ አይጥ እና ሌሎችም በሽታ አስተላላፊ እንሰሳትን ይስባል።
ጅቦች በፍጥነት የእንሰሳትን ቅሪት በመመገብ እና ቆሻሻን በማስወገድ በሽታን እንደሚከላከሉ ዶ/ር ግደይ ያስረዳሉ።
"ብዙ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅቦች በሚመገቡበት ቦታ ቆሻሻ በብዛት አይበሰብስም፤ ዝንቦችም ጥቂት ናቸው" ይላሉ።
ጅቦች ከየጎዳናው እና ከየሕዝብ አደባባዩ ቆሻሻ በማስወገድ የሰዎችን በበሽታ የመያዝ ዕድል ይቀንሳሉ። አካባቢን ንጹህ ማድረጋቸው የሰዎች ደኅንነት እንዲጠበቅ ያስችላል።
ጅቦች እንደ "አደገኛ እና የማይፈለጉ" እንሰሳት እንደሚወሰዱ አጥኚው ታዝበዋል። "ጥናታችን ግን የጅቦችን የተለየ ገጽታ ያሳያል" ይላሉ።
እነዚህ እንሰሳት በሺህ ቶኖች የሚቆጠር ቆሻሻ ያስወግዳሉ። የካርበን ልቀትን ከመቀነስ በተጨማሪ ንጽህናን ይጠብቃሉ።
"ብዙ ሰዎች ይሄንን እንደሚረዱ ጥናታችን ያሳያል። 72% ያህል ነዋሪዎች ጅቦች ጠቃሚ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ጥናቱ ይጠቁማል" ይላሉ ዶ/ር ግደይ።
ስለዚህም ጅቦችን እንደ ችግር ብቻ ከመመልከት፤ ሰዎች፣ እንሰሳት፣ ዕጽዋት እና ሌሎችም ነፍሳት የሚገኙበትን መስተጋብር (urban ecosystem) አካል አድርጎ በመቀበል "ዋጋቸውን ማየት" እንደሚያስፈልግ ይገልጻሉ።
አጥኚው ለዚህ ጥያቄ መልስ አላቸው። ከዚህ ቀደም ሚናቸው በደንብ አለመጠናቱ እምብዛም ጥቅም ላይ ላለመዋላቸው አንድ ምክንያት ነው።
የከተማ ዕቅድ (urban planning) እና የቆሻሻ አወጋገድ (waste management) ፖሊሲዎች በዋናነት በሰዎች እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ።
ከተሞች ዕቅድ ሲያወጡ "ሰዎች እና የዱር እንሰሳት በሰላማዊ መንገድ አብረው መቀጠል የሚችሉበትን መንገድ ባማከ
📌 Kaynak
Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.
Orijinal haberi oku →