ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 02.05.2026
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ከዘጠኝ ወር በፊት ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል።

እንደ እኔ ዓይነት በሽታ ያለበት ሌላ ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር የሚለው በረከት "ካሉም የማግኘት በጣም ጉጉቱ ነበረኝ" ሲል የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል።

ጤነኛ የሚባል የእርግዝና ጊዜ ያሳለፉት እናቱም ቢሆኑ ጀርባው ላይ 'እባጭ' ያለበት ልጅ ሲወልዱ በቀላሉ እንዳልተቀበሉት በረከት ይናገራል።

"ልጄን እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ሰይጣን ነው የሚል አስተሳሰብ ነው የነበራት፤ የመናፍስት ሥራ ነው ብላ ነበር የምታስበው፤ በጣም 'ትራውማታይዝድ' አድርጓት ነበር።"

የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው።

አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል።

ይህ በተለይ የቀኝ እግሩ ላይ ችግር እንዲያጋጥመው ማድረጉን የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ "በተለይ እያደግኩ ስመጣ እና ከስምንተኛ ክፍል በላይ ስሆን በርካታ ተግዳሮቶች ነበሩብኝ" ይላል።

እያደገ ሲመጣ ፊዚዮቴራፒስቶቼ እግሬን ለማጠናከር ብዙ እንቅስቃሴዎችን እንዲሠራ ይመክሩት ስለነበር እግር ኳስ እና ማርሻል አርት ያዘወትር የነበረው ዶ/ር ነቢያት እግሩ ላይ ተደጋጋሚ ቀዶ ሕክምና አድርጓል።

በአለርት፣ በጥቁር አንበሳ እና በኪዩር ሆስፒታሎች ተደጋጋሚ ቀዶ ሕክምና የተደረገለት ሲሆን፣ የቅርብ ጊዜ ቀዶ ሕክምናው የተደረገው ከሦስት ዓመት በፊት ነው።

"በሕክምና ውስጥ ማለፌ እናም ቤተሰቦቼም ያለውን ችግር በመረዳት ሕክምና ለመማር ፍላጎቱ የኖረኝ።"

ስፓይና ቢፊዳ አንድ ጊዜ ሕክምና ተደርጎ ተሽሎሃል ተብሎ ወደ ቤት የሚኬድበት አይደለም የሚለው ዶ/ር ነቢያት፣ የነርቭ መጎዳት ስላለው "እግሬ ላይ በተወሰነ መልኩ የነርቭ መድከሞች ነበሩ" ይላል።

በረከት ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ የቀዶ ሕክምና ያደረገው ከአስር ዓመት በፊት በ13 ዓመቱ መሆኑን ያስታውሳል።

በረከት በቅርቡ በነርሲንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። እርሱም ሕክምና ለማጥናት ምክንያት የሆነኝ ከስፓይና ቢፊዳ ጋር መወለዴ ነው ሲል ለቢቢሲ ገልጿል።

"በሕይወቴ አንድ የምፈልገው ነገር "ለምን?" ለሚለው ጥያቄዬ መልስ ማግኘት ነበር። ያንን ፍለጋ ነው ነርሲንግ ወደ መማር የገባሁት።"

ለምን ብሎ መጠየቅ የጀመረው ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ጀርባው ላይ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ፣ የሕክምና ባለሙያው 'በቃ እስካሁን ብዙ አይተናል፤ ምንም ዓይነት ለውጥ አይመጣም። ግን ከዚህ በኋላ ቀዶ ሕክምና የሚያደርግ ከሆነ ይህ ልጅ ይሞታል ወይንም ፓራላይዝ ይሆናል' ሲል መስማቱ ነው።

"በልጅነት አእምሮዬ የሆነ ወቅት እድናለሁ የሚል ሃሳብ ነበረኝ" የሚለው በረከት "ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሌላ በረከት የሚኖር፣ ዳይፐር መጠቀም የማቆም፤ ትምህርት ቤት 'ሙድ' የማይያዝበት በረከት የሚኖር መስሎኝ ነበር" ሲል የነበረውን ተስፋ ያስታውሳል።

ያ እንደማይሆን ሲረዳ ግን በረከት "መሰበሩን፤ በጣም መጎዳቱን" እና "ተስፋ መቁረጡን" ይናገራል።

"ለምን እንደዚህ ሆንኩ" የሚል ጥያቄ ራሱን ይጠይቅ የነበረው በረከት ዕድሜው ከፍ ሲል፣ በትምህርቱ ሲገፋ ሕክምና አጥንቶ የሕመሙን መንስዔ የበለጠ ለማወቅ ጣረ።

ስፓይና ቢፊዳ በአብዛኛው የሚከሰተው እናቶች ከእርግዝና በፊት እና በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ሰውነታቸው ውስጥ ፎሊክ አሲድ የሚባል የቫይታሚን እጥረት ሲከሰት ነው፡፡

በስፓይና ቢፊዳ የተጠቁ ሕጻናት እንደተወለዱ የሚታይ ያልተለመደ እብጠት በአብዛኛው ጊዜ ጀርባቸው፤ የራስ ቅላቸው እና ከኋላ አንገታቸው ላይ ይከሰታል፡፡

ለስፓይና ቢፊዳ መንስዔ የሚሆኑ አምስት ዓይነት ነገሮች መኖራቸውን የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በዋናነት ግን አንዲት እናት በደሟ ውስጥ በቂ ያልሆነ የፎሊክ አሲድ በሚኖርበት ጊዜ ጽንስ ሲፈጠር መሆኑን ያስረዳል።

"የጽንሱ ጭንቅላት እና ህብለሰረሰር የሚፈጠረው በ28 ቀን ውስጥ ነው" የሚለው ዶ/ር ነቢያት "በዚህ ወቅት እናትየው ነፍሰጡር ትሁን፤ አትሁን አታውቅም" ሲሉ ምን ያህል አሳሳቢ መሆኑን ይገልጻል።

"በእርግዝናው የ29ኛ ቀን የስፓይናል ኮርድ (ህብለሰረሰር) በመጠን እየተለቀ ይሄዳል እንጂ አይሠራም" የሚለው ዶ/ር ነቢያት፤ የቫይታሚን ቢ9 ወይንም ፎሊክ አሲድ እጥረት ያለባት እናት በስፓይና ቢፊዳ የተጠቃ ልጅ ልትወልድ ትችላለች።

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥናትን የሚጠቅሰው ዶ/ር ነቢያት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön