ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?

📌 Diğer 📰 BBC Amharic 🕐 27.04.2026
ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?

ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።

ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን የበላይነት የያዙበት ነበር። በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ የራሷን ክብረ ወሰን በማሻሻል ኬንያውያንን አስከትላ አሸንፋለች።

በወንዶች ውድድር ደግሞ ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።

በለንደን ማራቶን ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ በወንዶች ማራቶን ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

የ30 ዓመቱ ኬንያዊ ሰባስቲያን ሳዌ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት 59.30 ደቂቃ ብቻ ወስዶበታል።

ይህም ማለት ኬልቪን ኪፕቱም እንደ አውሮፓውያኑ በ2023 በ2:00:35 በማስመዝገብ ከያዘው ክብረ ወሰን በአንድ ደቂቃ የፈጠነ ነው።

በዓለማችን ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች እንደሚሮጥ ያሳየው እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ነው።

ነገር ግን ይህ ክብረወሰን የተገኘው ይፋዊ ባልሆነ እና ቁጥጥር በተደረገበት ሁኔታ ውስጥ ስለሆነ አልተመዘገበለትም።

በለንደን ማራቶን ሌላው አስደናቂው ነገር ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻም በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት መሆኑ ነው።

ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ በሴቶች ማራቶን የራሷን ክብረ ወሰን በማሻሻል 2:15:41 ገብታለች።

ልክ እንደሌሎች ብዙ ስፖርቶች የረዥም ርቀት ሩጫ በስልጠና ስርዓቶች፣ በአመጋገብ እና በመሳሪያዎች መሻሻል ተጠቃሚ ሆኗል።

በተለይም ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ተወዳዳሪዎች ፈጣን ውጤቶችን ከሚያስገኙ፣ በክብደት ቀላል ከሆኑ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ከታከለባቸው ጫማዎች በብዙ ተጠቅመዋል።

ለምሳሌ የወንዶች የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ከአራት ደቂቃዎች በላይ ተሻሽሏል። በሴቶችም ዘንድ በተመሳሳይ ፍጥነት የተከሰተ ነው።

እነዚህን የማራቶን ክብረ ወሰኖች ልዩ የሚያደርጋቸው ውጤቶቹ የተመዘገቡት በተመሳሳይ የውድድር መስክ ከጥቂት አገራት በመጡ አትሌቶች መሆናቸው ነው።

ባለፉት አምስት ኦሎምፒኮች የኬንያ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ከ800 ሜትር ጀምሮ በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች አብዛኛዎቹን ሜዳሊያዎች አሸንፈዋል።

በወንዶች ማራቶን ውድድር ከ20ዎቹ ፈጣን ሯጮች ውስጥ ሁለቱ ብቻ በኬንያዊ ወይም በኢትዮጵያዊ ሯጭ አልተመዘገቡም።

በሴቶች ማራቶን ውድድር ከ20ዎቹ ፈጣን ሯጮች ውስጥ 18ቱ ከእነዚህ ሁለት አገሮች የመጡ አትሌቶች ናቸው።

ለአሸናፊነታቸው ወሳኝ ከሆኑት ነገሮች መካከል በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ የሚገኘው ተራራማ አካባቢ አንዱ ነው።

ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ባላቸው ከተሞች እና መንደሮች የሚኖሩ ሯጮች፣ በተለይም እዚያ የተወለዱት፣ ከፍተኛ ከፍታ ባላቸው ቦታዎች እና ዝቅተኛ የኦክስጅን መጠን ባለበት ስፍራ ልምምድ ሲያደርጉ የልብና የሳንባ ጥንካሬን ያዳብራሉ።

ይህ በእርግጥ ለስኬት ዋስትና አይሆንም። እንደ ኔፓል እና ቦሊቪያ ባሉ ተራራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ያሏቸው አገሮች አሉ።

ኬንያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን የሚለያቸው ሩጫ በትውልዶች መካከል በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ መቀረጹ ነው።

ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ሯጭ ኃይሌ ገብረስላሴ ልጅ በነበረበት እና ረዥም ርቀት በእግር መጓዝ ልማድ ከነበረበት ዘመን ወዲህ በአፍሪካ በከፍተኛ ፍጥነት ከተሜነት እና ከተማ ማደጉን አስተውሏል። ነገር ግን ሩጫ በኢትዮጵያ እና በኬንያ ዘንድ የባሕሉ አካል ሆኖ ቀርቷል።

በኬንያ ለብዙ ዓመታት የኖረውና የሠራው የቀድሞ የስፔን ሯጭ ማርክ ሮይግ፣ ልጆቹ በተማሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ ስለ ሩጫ ሲያወራ ሌሎች ወላጆች ያለመደነቅ ይሰሙት እንደነበር ያስታውሳል። ሮይግ እየቀለደ ሩጫ ባሕል በሆነበት አገር "ከእንግዲህ እዚያ ሯጭ ነኝ አልልም" ይላል።

ስፔናዊው በአሁኑ ጊዜ ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ በስተሰሜን 260 ኪ.ሜ. እና ከባህር ጠለል በላይ 2400 ሜትር ከፍታ ላይ በምትገኘው ኢተን ከተማ ውስጥ ታዳጊ ሯጮችን የሚያሰለጥን ፕሮጀክትን በበላይነት ይቆጣጠራል።

ኢተን በአካባቢው "የአሸናፊዎች መኖሪያ" በመባል ትታወቃለች። ምክንያቱም የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊዎችን ጨምሮ ለብዙ ታዋቂ የኬንያ ሯጮች መገኛ ስፍራ ናት።

ሮይግ እንደሚለው የአካባቢው ታዳጊዎች ዝናቸው በየዕለቱ የሚነገርላቸው ውጤታማ አትሌቶች የኖሩት በአቅራቢያቸው ነው።

ጎዳናዎቹ እነዚህ ብርቅዬ አትሌቶች የሮጡበት መሆኑ ይህም በየዕለቱ በሚሰሙት የውጤታማነት ታሪክ መታጀቡ እነርሱንም ወደ ሩጫ እንዲሳቡ ያደርጋቸዋል።

በተለይም ድህነት አሁንም ብዙዎችን እግር ተወርች በያዘበት አገር እና አህጉር ውስጥ መሆን ጥሩ ገንዘብ የማግኛ ተስፋም ይሆ

📌 Kaynak

Bu özet BBC Amharic kaynağından otomatik derlenmiştir. Tamamı için orijinal habere gidin.

Orijinal haberi oku →
← Tüm haberlere dön